ከኢየሱስ በፊት እንደነበሩ ነብያቶች ሁሉ የኢየሱስ ወይም የኢሳ (ዐ.ሰ) ሃማኖት እስልምና ብቻ ነው። ኢየሱስም በአንድ አምላክ ብቻ የሚያምን እና አንድ አምላክ ብቻ የሚገዛ ነበር።
በመጽሐፍ ቅዱስ ኦሪት ዘዳግም 6:4 ላይ “እስራኤል ሆይ! ስማኝ ጌታችን አምላካችን አንድ አምላክ ነው።” ብሏል። ማርያምም ሆነች ልጇ ኢየሱስ ያመልኩት (ይገዙት) የነበረው አንድ አምላክ ብቻ ነው።
ሆኖም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ኢየሱስ ከእሱ በፊት ለነበሩ ነብያት የተገለጠላቸውን ሰማያዊ ህግ እና ስርአተ አምልኮ ሊሽር ያልመጣ መሆኑን ይናገራል።
መጽሐፍ ቅዱስ
(የማቴወስ ወንጌል 5:17-18)
“እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።”
እንዲህም ብሏል:
መጽሐፍ ቅዱስ
(የዮሐንስ ወንጌል 20:17)
“ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው።”
ይቀጥላል
መልዕክቱ ቢያንስ ለሶስት ሰው ሼር አድርጉት


