መግቢያ
በህይወት ማዕበል ውስጥ ሁሉም ነገር የሚናድ ሲመስል ተስፋ መቁረጥ ይቀላል። ፈተናዎች ሲደራረቡ “እንዴት አልፋለሁ?” የሚለው ጥያቄ ልብን ያከብዳል። ነገር ግን ለአንድ ሙስሊም ፣ ይህ የተስፋ መቁረጥ ሰዓት ሳይሆን ወደ አላህ ይበልጥ የምንቀርብበት ወርቃማ አጋጣሚ ነው። ይህ ጽሑፍ በችግሮች ውስጥ የተደበቀውን ጥልቅ ትርጉም በመረዳት እንዴት የፀና እምነት መገንባት እንደምንችል ያስቃኘናል።
ከእያንዳንዱ መከራ ጀርባ ያለውን መለኮታዊ ጥበብ ፣ የ”ሶብረን ጀሚል” (ውብ ትዕግስት) ሚስጥር እና በአሸናፊው ጌታ ላይ የመመካትን ጣፋጭ ፍሬ በማስተዋል ፣ በፈተናዎች ውስጥ ወደማይናወጥ መረጋጋትና ውስጣዊ ጥንካሬ እንዴት እንደምንደርስ እናያለን።
ለምን ሙስሊም በፈተና ጊዜ ይለያል?
በህይወትህ ውስጥ አስቸጋሪ ጊዜን እያሳለፍክ ነው… ሁሉም ነገር እያየኸው የሚፈራርስ ይመስላል።
ተስፋ እየቆረጥክ ነው… እናም “በዚህ ሁኔታ እንዴት መኖር እችላለሁ?” ብለህ እራስህን ትጠይቃለህ።
የሚያጋጥሙህ መሰናክሎች ሁሉ በሃይላቸው ወደ ታች ይጎትቱሃል። አንተ ግን ከሌሎቹ ሁሉ ትለያለህ… ምክኒያቱም አንተ ሙስሊም ነህና።
ኃያሉ አላህ ጉዳይህን ሁሉ እንደሚያስተካክልልህ ታውቃለህ። ይህንንም የምታውቀው ከስውር ዓለም ቀጫጭን መጋረጃዎች ጀርባ አይደለም፤ ይልቁንም በገሃድ ከተገለጸው የጌታህ ቃል ነው።
የአላህ ተስፋዎች፡ ከችግር ጋር ምቾት አለ
አል-ቁርአን
(አል-ኢንሺራሕ 94:5)
“ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ”
ባለ ጊዜ፣ አንተን በቀጥታ እያነጋገረህ እንደሆነ በልብህ ታውቃለህ። እሱ ምርጥ የሆኑ አማኝ ባሮቹን በተለያዩ ፈተናዎች እንደሚፈትንም ተረድተሃል። ከእያንዳንዱ ፈተና በስተጀርባ የተደበቀ ጥበብ እንዳለ ታምናለህ፤ ይኸውም፡
አላህ (ሱ.ወ) በቅዱስ ቁርአኑ
አል-ቁርአን
(አል-ኢንሺራሕ 94:5)
“ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አለ”
ባለ ጊዜ አንተን በቀጥታ እያነጋገረህ እንደሆነ በልብህ ታውቃለህ። እሱ ምርጥ የሆኑ አማኝ ባሮቹን በተለያዩ ፈተናዎች እንደሚፈትንም ተረድተሃል። ከእያንዳንዱ ፈተና በስተጀርባ የተደበቀ ጥበብ እንዳለ ታምናለህ፤ ይኸውም፡
- ደረጃ ከፍታ፡ ከእያንዳንዱ ፈተና ጋር፣ እሱ ዘንድ ያለህ ደረጃ ከፍ ይላል።
- የነፍስ ንፅህና፡ ነፍስህን ከኃጢአት ያጠራላታል፣ ያነፃላታል።
- የኢማን ጣዕም፡ ሙወሒዶች (አላህን በአንድነት የሚያመልኩ) እንጂ ሌላ ማንም ሊደርስበት የማይችለውን ልዩ የሆነውን የኢማንን ጣዕም ይለግስሃል።
የነብያትና የቀደምት ደጋጎች ፈተና
ይህን ታውቃለህ ምክኒያቱም መልዕክተኛህን (ሰ.ዐ.ወ) ከስውር ዓለም ቀጫጭን መጋረጃዎች ጀርባ ሆነህ ስላየሃቸው ነው፡፡ ያጋጠሟቸውን መከራዎች ሰምተሃል፡፡ ስለ ተከበሩ ሶሃቦቻቸው አንብበሃል… ስለ ምርጥ ቀደምት ትውልዶች እንዲሁ… ያለፉበትን ችግር እና መከራ ተምረሃል።
አሁን የሚያጋጥሙህ ችግሮች በአሏህ ፈቃድ አንድ ቀን እንደሚወገዱ በእርግጠኝነት ታውቃለህ፤ ልክ ሞቃቷ የፀሐይ ብርሃን ከድቅድቁ የሌሊቱ ጨለማማና ሰዓታት በኋላ እንደምትወጣ እንደምታውቀው ሁሉ ማለት ነው።
ስለዚህ ከአድማስ ባሻገር የፀሐይ ብርሃን ስትወጣ እየተመለከትክ የምትፈልገውን መረጋጋት (ሰኪና) እንድታገኝ የምታልፍበትን ፈተና ለመቋቋም ዝግጁ ሁን።
የሶብረን ጀሚል (ውብ ትዕግስት) ሚስጥር
ሁሉም ነገር ደረጃ በደረጃ እንደሚከሰት ታውቃለህ፤ ጭንቀትም “የደስታ ጥግ” ብለህ ወደምታስበው ነገር የምትደርስበትን ፍጥነት እንደማይጨምርልህ ታውቃለህ… ስለዚህ ውብ ትዕግስት (ሶብረን ጀሚል) መላበስ ይገባሃል።
ቅሬታ መቅረብ ያለበት ለሃያሉ አሏህ ብቻ እንደሆነ የፀና እምነት ላይ ደርሰሃል፡፡ በብዛት ብትጠይቀውና ከፊቱ ቅሬታህን ብታቀርብ የማይሰለችህ እሱ ብቻ ነው።
የሚያጋጥምህ ነገር ምንም ይሁን ምን አዎንታዊነት መፍትሔ ወደሆነው እምነት ደርሰሃል…። እነዚህ ሁሉ ክስተቶች በህይወትህ ውስጥ አስፈላጊ የሆኑ የመማሪያ እድሎችህ ናቸው።
በአሏህ ላይ ተመካ
ወደ አንድ የፀና እምነት ላይ ደርሰሃል፤ ይኸውም ወደፊት ትጓዛለህ ምክንያቱም ይህች ህይወት አጭር እና ጊዜያዊ ህይወት ናትና።
“ሙስሊም” መሆንህ ፣ መመካትህና መደገፍህ (ተወኩል) በአሸናፊውና በጥበበኛው አሏህ ላይ ስለሆነ ወደ ፀና እምነት ደርሰሃል። ምንዳህ ታላላቅ ምንዳዎችን ከሚሰጠው ከአሏህ ነው።
ማጠቃለያ
በማጠቃለያው ፣ እያንዳንዱ ፈተና የቅጣት ምልክት ሳይሆን ፣ ወደ አላህ የምንቀርብበት ፣ ነፍሳችንን የምናጠራበትና የኢማናችንን ጥልቀት የምንፈትንበት አጋጣሚ ነው።
በውብ ትዕግስት (ሶብረን ጀሚል) እና በአላህ ላይ ሙሉ በሙሉ በመመካት (ተወኩል) ስንጸና፣ በችግር ውስጥ የተደበቀውን መረጋጋትና ድል እናገኛለን።
ይህ የፀና እምነት ፣ ጊዜያዊ በሆነው የዱንያ ህይወት ውስጥ ዘላለማዊ የሆነውን ስኬት እንድናስብ ያስችለናል።
በዚህ ርዕስ ላይ የእርስዎ ተሞክሮና አስተያየት ምንድን ነው? ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ሳጥን ላይ ያጋሩን።
Share