የቅዱስ ቁርአን ፍች

Author picture
ይህ የቅዱስ ቁርአን ፍች ትምህርት ተማሪዎች የቅዱስ ቁርአንን እውነታዎችን በአይነህሊና እንዲያዩ ፣ እንዴት እንደተገለጠ እና የቁርአንን የአሰባሰብ ሂደት እንዲያውቁ ይረዳል።

የትምህርቱ አጭር መግለጫ

ይህ የቅዱስ ቁርአን ፍች ትምህርት ተማሪዎች የቅዱስ ቁርአንን እውነታዎችን በአይነህሊና እንዲያዩ ፣ እንዴት እንደተገለጠ እና የቁርአንን የአሰባሰብ ሂደት እንዲያውቁ ይረዳል።

የጽሁፉ አላማ

  1. ስለ ቅዱስ ቁርአን እውነታዎች ፣ ስለ ክፍሎቹ እና ስለ ምዕራፎቹ ትማራላችሁ
  2. የቅዱስ ቁርአን የአስተሳሰብ ሂደቶቹን ትማራላችሁ

ቅዱስ ቁርአን

ሃያሉ አሏህ ቁርአን የገለጠው ከፍጡራኖቹ ሁሉ በላጭ ለሆኑ እና ለነብያት መደምደሚያ ለሆኑት ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ነው። ቁርአን ለሰው ልጆች ሁሉ መመሪያ እና ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገሪያ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡

“በእርግጥ ከአሏህ ዘንድ ብርሃን እና ገላጭ መጽሐፍ መጣላችሁ። አሏህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች የሰላምን መንገድ በእሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማ ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛውም መንገድ ይመራቸዋል።”
(ሱረቱል ማኢዳ 15-16)

የቅዱስ ቁርአን ትርጉም

ቅዱስ ቁርአን ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለጠላቸው ተአምራዊ ቃል ነው። ቁርአን በፋቲሃ ጀምሮ በሱረቱ አናስ የሚያበቃ ሲሆን ይህን በማንበብም አሏህ ይመለክበታል።

ቁርአን ክብሩን እና ቱሩፋቱን የሚያመላክቱ ብዙ ስሞች አሉት። ከእነዚህ ስሞች ውስጥ

1 ቁርአን፡ ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ “ይህ ቁርአን ወደዚያች ቀጥተኛ ወደ ሆነችው መንገድ ይመራል።” (ሱረቱል ኢስራ 9)

2 መጽሐፉ፡ ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡ “ይህ በውስጡ ጥርጣሬ የሌለበት መጽሐፍ ነው።” (ሱረቱል በቀራ 2)

3 አል-ፉርቃን፡ ሃያሉ አሏህ እንዳለው፡ “ፉርቃንን በባሪያው ላይ ያወረደው (አምላክ) ክብር እና ጥራት ተገባው።” (ሱረቱል ፉርቃን 1)

4 ዚክሩ፡ ሃያሉ አሏህ እንዳለው፡ “በእርግጥ ዚክሩን (አስታዋሹን) አወርድነው፤ በእርግጥ እኛም  እንጠብቀዋለን።” (ሱረቱል ሒጅር 9)

የቅዱስ ቁርአን መገለጥ

ቁርአን መጀመሪያ ለነብዩ (ሰ.ዐወ) የተገለጠው በረመዷን ውስጥ በለይለቱል ቀደር (በውሳኔዋ ሌሊት) ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡

“ያ በእሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩ ገላጭ (አንቀፆች) ሲሆኑ ቁርአን የወረደበት የረመዷን ወር ነው።”
(ሱረቱል በቀራ 185)

ቁርአን ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከአሏህ የተገለጠላቸው ከተከበሩ መልአክቶች ውስጥ አንዱ በሆነው በመልአኩ ጅብሪል አማካኝነት ነው። ሃያሉ አሏህ ስለ ቁርአን እንዲህ ይላል፡

“በእርግጥ እሱ (ቁርአን) ከአለማት ጌታ የወረደ ነው። በታማኙ መንፈስ (ጅብሪል) አወረደው። ከአስጠንቀቃቂዎች (ነብያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ አወረደው። ግልፅ በሆነ አረብኛ ቋንቋ።”
(ሱረቱ አሹአራ ፡ 192-195)

ከቁርአን ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለጠላቸው የመጀመሪያው ራዕይ የሱረቱል አለቅ የመጀመሪያዎቹ አምስት አንቀፆች ናቸው። ተከታዩ የአሏህ ንግግር ነው።

“በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም አንብብ። የሰውን ልጅ ከአለቅ (ከረጋ ደም) በፈጠረው ጌታህ ስም። አንብብ! ጌታህ በጣም ቸር ሲሆን ያ በብዕር ያስተማረ። የሰው ልጅ ያለወቀውን ሁሉ ያሳወቀ በሆነው።”
(ሱረቱል አለቅ 1-5)

ከዚያ በኋላ ቁርአን መካ እና መዲና ውስጥ እንደነበረው ነባራዊ ሁኔታ እና የሁነቶች ክስተት ጋር በተያያዘ እና በተለያዩ ጊዜያት በሃያ ሶስት አመታት ውስጥ ለነበዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተገለጠ።

ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንደህ አለ፡ ‹‹ቁርአን በአንድ አረፍተ ነገር ወደ ሰማኡ ዱንያ (ወደዚህ አለም ሰማይ) የወረደው በለይለቱል ቀድር (በውሳኔዋ ሌሊት) ነው።

ከዚያም በኋላ በሃያ ሶስት አመታት ውስጥ ተገለጠ።›› (አልበይሃቂ፡ ስሞች እና ባህሪያት 497)

የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች

የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች 114 ናቸው። ሆኖም የመጀመሪያው ምዕራፍ አል-ፋቲሃ ሲሆን የመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ አል-ናስ ነው።

የመካ እና የመዲና ምዕራፎች

1 የመካ ምዕራፎች 86 ሲሆኑ የተገለጡትም ነብዩ (ሰ.ዐወ) ወደ መዲና ከመሰደዳቸው በፊት ነው።

2 የመዲና ምዕራፎች 28 ሲሆኑ የተገለጡትም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከተሰደዱ በኋላ ነው።

የቁርአን ክፍሎች 30 ሲሆኑ ሂዝቡ ደግሞ 60 ናቸው።

0%
13
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

የቁርአን ጥያቄና መልስ

1 / 10

Bookmark question icon

1 ቁርአን የተገለጠው (የወረደው) በስንት ዓመታት ውስጥ ነው?

2 / 10

Bookmark question icon

2 ከነብዩ ሰሃቦች (ባልደረቦች) መካከል በቁርአን ውስጥ በስም የተጠቀሰው ብቸኛው ሰሃባ ማን ነው?

3 / 10

Bookmark question icon

3 በቁርአን ውስጥ “ቢስሚላሂ-ራህማኒ-ራሂም” (በስመ አላህ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው) ብላ የማትጀምረው ብቸኛዋ ሱራ (ምዕራፍ) የትኛዋ ናት?

4 / 10

Bookmark question icon

4 በቁርአን ውስጥ እያንዳንዱ አንቀጽ (አያህ) “አላህ” የሚለውን ስም የያዘው ሱራ የትኛው ነው?

5 / 10

Bookmark question icon

5 በአጠቃላይ በቁርአን ውስጥ ስንት ሱራዎች አሉ?

6 / 10

Bookmark question icon

6 “ሰጅደቱ-ቲላዋ” (የንባብ ስግደት) በቁርአን ውስጥ በስንት ቦታዎች ላይ ይገኛል?

7 / 10

Bookmark question icon

7 በቁርአን ውስጥ በብዛት የተጠቀሰው ነብይ ማን ነው?

8 / 10

Bookmark question icon

8 በቁርአን ውስጥ በነብይ ስም የተሰየሙ ስንት ሱራዎች አሉ?

9 / 10

Bookmark question icon

9 “አያተል ኩርሲ” (የዙፋኑ አንቀጽ) የሚገኘው በየትኛው የቁርአን ሱራ ውስጥ ነው?

10 / 10

Bookmark question icon

10 ከቁርአን አንድ ሶስተኛ (1/3) ጋር እኩል እንደሆነች የሚነገርላት ሱራ የትኛዋ ናት?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 23%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

የቁርአን ጽህፈት እና አሰባሰብ

የቅዱስ ቁርአን ጽህፈት እና አሰባሰብ ሶስት ደረጃዎች አሉት።

የመጀመሪያው ደረጃ፡ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን

በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ትኩረቱ የነበረው ከመፃፍ ይልቅ ሽምደዳ ላይ ነው። ለዚህ ምክኒያቱ ደግሞ የመሸምደድ አቅማቸው እና ለመሸምደድ የነበራቸው ፍጥነት ጠንካራ በመሆኑ ፣ የጽሐፊዎች እና የመፃፊያ ዘዴ ባለመኖሩ ምክኒያት በመጽሐፍ መልክ አልተሰበሰበም ነበር።

ነገርግን አንድ አንቀፅ በሰሙ ጊዜ ይሸመድዱ እና ባገኙት የዘንባባ ዛፍ ጉማጅ ፣ ብራና እና ድንጋይ ላይ ይፅፉ ነበር።

ሁለተኛው ደረጃ፡ በአቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) ጊዜ

በአስራ ሁለተኛው አመተ ሂጅራ በየማማ ጦርነት ጊዜ ብዙ ቃሪኦች (አንባቢዎች) በመገደላቸው ምክኒያ እና ቁርአን እንዳይጠፋ በማሰብ ቁርአኑ እንዲሰበሰብ አቡበክር (ረ.ዐ) አዟል።

ዘይድ ኢብኑ ሳቢት (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹የየማማ ሰዎች (በሙሰይሊማ) በተገደሉ ጊዜ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) መልዕክት ላከብኝ። እኔም ወደ እሱ ሄድኩ። እናም ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ከእሱ ጋር ተቀምጦ አገኘሁት። አቡበክር (ረ.ዐ) እንዲህ አለኝ፡ ‹‹በየማማ የጦር ሜዳ ቁርአን አንባቢዎች ላይ የደረሰው ሞት የከፋ እንደሆነ ኡመር (ረ.ዐ) ነግሮኛል። በሌላ የጦር ሜዳ ተጨማሪ የቁርአን አንባቢዎች እንዳይሞቱ እና ከፍተኛው የቁርአን ክፍል እንዳይጠፋ እሰጋለሁ። ሆኖም ቁርአን እንዲሰበሰብ አቡበክር ትዕዛዝ እንዲያስተላልፍ ሃሳብ አቀረበ። ለኡመርም እንዲህ አልኩት፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ያላደረጉትን አንተ ታደርጋለህን? አልኩት። ኡመርም ያ ጥሩ ፕሮጀክት ነው አለ። አሏህ ለዚህ ነገር ደረቴን እስከከፈተልኝ ጊዜ ድረስ ኡመር ያቀረበውን ሃሳቡን እንድቀበል ጎተጎተኝ። ኡመር የተረዳውን ሃሳብ እኔም መረዳት ጀመርኩ። ከዚያም አቡበክር ‹‹አንተ ጠቢብ ወጣት ነህ፤ በአንተም ላይ አንዳችም ጥርጣሬ የለንም። ለአሏህ መልዕክተኛ የተገለጠላቸውን መለኮታዊ ራዕይ ትፅፋለህ። ሆኖም የተበታተኑ የቁርአን የእጅ ጽሁፎችን አፈላልገህ በአንድ መጽሐፍ አሰባስበው አለኝ።

በአሏህ ይሁንብኝ! ከተራራዎቹ አንዱን እንዳንቀሳቅስ ቢያዙኝ ይህን የቁርአን እንዳሰባስብ ካዘዙኝ የበለጠ የሚከብድ አይመስለኝም። ከዚያም ለአቡበክር እንዲህ አልኩት፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ያላደረጉትን ነገር እናንተ ታደርጋላችሁን›› አልኩት። አቡበክርም፡ ‹‹በአሏህ ይሁንብኝ ጥሩ ፕሮጀክት ነው›› ሲል መለሰልኝ። አሏህ የአቡበክር እና የኡመርን ደረት እንደከፈተው የእኔንም ደረት እስከከፈተልኝ ድረስ አቡበክር ሃሳቡን እንድቀበል ጎተጎተኝ። ከዚያም ቁርአንን መፈለግ ጀመርኩ።

የሱረቱ ተውባን የመጨረሻውን አንቀፅ ከአቢ ኸዛኢም አል-አንሷሪ እንጅ ከእሱ በቀር ከሌላ ሰው ማግኘት እስካልቻልኩበት ጊዜ ድረስ በተለያዩ ነገሮች ላይ በዘንባባ ዛፍ ጉማጆች ፣ በነጭ ድንጋይ ላይ እና በልባቸው ካስቀመጡ (ከሸመደዱ) ሰዎች አሰባሰብኩ። ከዚያም ሙሉ የቁርአን የእጅ ፅሁፍ ቅጅ አቡበክር እስኪሞት ድረስ ከእሱ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም ኡመር እስኪሞት ድረስ ከእሱ ጋር ተቀመጠ። ከዚያም የኡመር ልጅ ከሆነችው ሐፍሷ ጋር ተቀመጠ።›› (ቡኻሪ 4986)

ሶስተኛው ደረጃ፡ በኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዐ) ዘመን

በኡስማን ቢን አፋን (ረ.ዐ) የአስተዳደር ዘመን የእስልምና የግዛት ወሰን ተስፋፍቷል። የሁሉም ሐገር ሰዎች ከሶሃቦች መካከል ያስተማሯቸውን የቁርአን የአነባበብ ዘይቤ ተቀበሉ።

በቅዱስ ቁርአን የአነባበብ ዘይቤ ብዝሃነት ምክኒያት እና ቅዱስ ቁርአንን ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያልሰሙ ሰዎች እንዳይሳሳቱም ተፈራ።

እናም ሰዎች በሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ላይ እንዳይለያዩ ፣ እንዳይጨቃጨቁ እና እንዳይበታተኑ በማሰብ ኡስማን (ረ.ዐ) ሰዎች ሰዎች በአንድ የቁርአን ቅጅ እንዲሰባሰቡ አዘዘ።

አነስ ኢብን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ሁዘይፋ ቢን አልየማን ወደ ኡስማን መጣ። በአርመን ወረራ ወቅት የሶሪያን ሰዎች ሲዋጋ ፣ አዘርባይጃን ደግሞ ከኢራቅ ሰዎች ጋር ሲዋጉ በነበራቸው የአነባበብ ልዩነት ምክኒያት ኹዘይፋ ፈራ። እናም ኹዘይፋ ለኡስማን እንዲህ አለው፡ ‹‹የሙዕሚኖች አዛዥ ሆይ! አይሁዳዎች እና ክርስቲያኖች እንደተለያዩት ሁሉ ይህ ኡማ በመጽሐፉ ከመለያየታቸው በፊት ተረዳቸው አለው።

እናም ‹‹በመጽሐፍ መልክ እናበዛቸው ዘንድ ቅጅውን ላኪልን፤ ከዚያም መልሰን እንልክልሻለን›› ሲል ኡስማን ወደ ሐፍሷ መልዕክት ላከ። ሐፍሷም ወደ ኡስማን ቅጅውን ለከች። ከዛም ዘይድ ቢን ሳቢት ፣ አብዱ ረህማን ቢን አል-ሐሪስ ቢን ሂሻምን በቁርአን ማባዛት ሂደት ውስጥ እንዲካተቱ እና ቁርአኑን እንዲያባዙ አዘዛቸው።›› (ቡኻሪ 4987)

እስከ አሁኗ ጊዜ ድረስ ቁርአን ያኔ በተሰበሰበበት ሁኔታ እና ሙስሊሞች በተስማሙበት ሁኔታ ተጠብቆ ቆይቷል።

0%
3
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

ጥያቄና መልስ፡ የቅዱስ ቁርአን መግቢያ

የቅዱስ ቁርአን መግቢያ ፈተና 6 ጥያቄዎችን የያዘ ሲሆን ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ቅዱስ ቁርአን በመጽሐፍ መልክ የተሰበሰበው ______ የአስተዳደር ዘመን ነበር።

2 / 6

Bookmark question icon

2 የቅዱስ ቁርአን ምዕራፎች ስንት ናቸው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 ቁርአን ከሃያሉ አሏህ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የወረደው ______ አማካኝነት ነው።

4 / 6

Bookmark question icon

4 ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጀመሪያ ላይ የተገለጠላቸው ራዕይ በየትኛው ወር ውስጥ ነበር?

5 / 6

Bookmark question icon

5 ከቁርአን መጠሪያ ስሞች ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 ሃያሉ አሏህ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የገለጠላቸው መጽሐፍ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 26%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ቁርአን የደመና እና የዝናብ አፈጣጠርን በተመለከተ ምን ይላል

አላህ እንዲህ ይላል፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- “ነፋሶችንም ለምለም አድርገን ላክን፤ ከሰማይም ውሃን አወረድን፤ ከእርሱም አጠጣናችሁ፤ እናንተም ለእርሱ አከማቾች አይደላችሁም።” (አል-ቁርአን15:22) ዘመናዊ ሳይንስ በነዚህ የቁርአን አንቀፆች

Read More »

ቁርአን ስለ ሰው ልጅ ሽል ደረጃዎች

ፅንስ የሚያልፍባቸውን ደረጃዎች በተመለከተ አላህ እንዲህ ይላል፡- አንድ ሰው የሚያልፍባቸው ደረጃዎች፡- ከጭቃ ንጥር፡ የሰው ልጅ አባት የሆነው አደም ከጭቃ ተፈጥሯል። ይህ የሚያመለክተው ሰዎች የተለየ ፍጥረት

Read More »

ቁርአን ስለ ከባቢ አየር

ቁርአን ስለ አየር ግፊት ምን ይላል አላህ እንዲህ ይላል፡- ከዚህ አንቀጽ መረዳት እንደሚቻለው አንድ ሰው ወደ ከባቢ አየር በወጣ ቁጥር መተንፈስ እየከበደው ይሄዳል። ይህም በከባቢ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share