ቤትህ ይስፋህ! ከተንኮለኞችና ከስራ ፈቶች በመራቅ ሸሪዓዊ ብቸኝነትን በመተግበር የህሊና እረፍትንና ውስጣዊ ሰላምን ያግኙ። ይህ ጽሁፍ እንዴት ቤትዎ በመቀመጥ እራስዎን መጠበቅና ማደግ እንደሚችሉ ያሳየዎታል።

ሸሪዓዊ እና ሱናዊ ብቸኝነት፤ ከተንኮልና ከተንኮለኞች መራቅህ ፣ ከስራፈቶች ፣ ከቦዘኔዎች እና ከሁከት ፈጣሪዎች መገለልህ ስብስብ ማለት መቻልን ፣ የህሊና እረፍትን ፣ መረጋጋትንና ህሊናህ በጥበብ ፈርጦች እንዲዳብርና ዓይኖችህም በእውቀት አፀድ ላይ እንዲዘዋወሩ ይረዳሃል።

ከመልካም ስራዎችና ጌታን ከመታዘዝ ከሚያግዱ ነገሮች ሁሉ ተገልሎ ብቸኛ መሆን የልብ ሃኪሞች በተሞክሮ የደረሱበት ፍቱን ፈውስ ነው። እኔም ወደ እሱ አመላክትሃለው።

ከተንኮል፤ ከውድቅ ሦራዎች እና አላስፈላጊ ስብስቦች መራቅ አእምሮን ያዳብራል ፣ የአሏህን ፍራቻንም ያመጣል ፣ አሏህን የማውሳትና የመዘከር ውዴታን ያስከትላል።

ምስጉን ስብሰባዎችንና የተወደሱ ቅልቅሎች ሊባሉ የሚችሉት ለአምስቱ የሶላት ጊዜያት፤ በጁምአ ሶላት፤ በዕውቀት መድረኮች እና በመልካም ስራዎች ላይ ለመተባበር የሚደረጉ መሰባሰቦች ሲሆኑ፤ የስራፈቶች እና የዛዛታ አራማጆች ስብሰባዎችን ግን ተጠንቀቅ ሽሽም።

በወንጀልህ አልቅስ ፣ ምላስህንም ቆጥብ ፣ ቤትህ ይስፋህ። አልባሌ ቅልቅሎች በነፍስ ላይ የሚካሄዱ ጦርኖቶች ናቸው።

በነፍስህ ውስጥ የሰፈኑ የመረጋጋትና የሰላም ስሜቶች ላይ ጦርነት እንደመክፈት ነው። ምክንያቱም እነርሱ የአሉባልታ ነገስታት እና የወሬ ጀግኖች ናቸው።

እንዲሁም በመከራ ፣ አደጋና ፈተና የሚያበስሩ መጥፎ የገድ መምህራን ናቸው። ሞት ሳይመጣብህም በቀን ሰባት ጊዜ የሞትክ ያህል እንዲሰማህ ለማድረግ ይጥራሉ።

አል-ቁርአን

{ሱረቱ ተውባ 9:47}

«ከናንተ ጋር በወጡ ኖሮ ጥፋትን እንጂ አይጨምሩላችሁም።»

ስለዚህ ከአንተ የምፈልገው ብቸኛው ምኞቴ ሙሉ ትኩረትህን በራስህ ጉዳዮች ላይ እንድታደርግ ፣ ለመልካም ንግግር እና ተግባር ሲቀር ቤትህ ውስጥ እንድትሆን ነው።

የዚያኔ ቀልብህ ተመልሶልህ ታገኘዋለህ። ስለዚህ ጊዜህን ከጥፋት ጠብቀው። እድሜህንም ከመግደል ፣ ምላስህን ከሃሜት ፣ ልብህን ከጭንቀት ፣ ጆሮህን ከአፀያፊ ቃላት ፣ ነፍስህንም ከመጥፎ ጥርጣሬ ጠብቅ።

እነዚህን የተገበረ እውነታውን ይረዳል። ነፍሱን በውድቅ ምግባሮች ጀርባ ላይ ላስጋለበ ሰው፤ ከሥራፈቶቹም ጋር ጊዜውን ላሳለፈ………..ደህና ሁን በልልኝ።

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share