ሙዝደሊፋ

ሙዝደሊፋ በሚና እና በአረፋ መካከል ያለ ቦታ ነው። አል-መሽአር ፣ አል-ሐረም (ቅዱሱ ቋጥኝ) እና አል-ጀም (መሰብሰቢያው) ተብሎ ይጠራል። ምክኒያቱም ሁጃጆች በ10ኛው የዙል ሂጃ ወር ከአረፋ እንደተመለሱ በዚሁ ቦታ ይሰባሰባሉና ነው።

ምሽቱን ሙዝደሊፋ ውስጥ ማሳለፍ ግዴታ ነው። ይህ ያመለጠው ሰው የእርድ እንስሳ መስዋዕት በማድረግ ማካካስ አለበት።

በ9ኛው ዙልሂጃ ፀሐይዋ ከጠለቀች ቡኋላ አረፋ ለቀው በመውጣት ፀጥ ብለው ጦልቢያ እና ሌሎች ፀሎቶችን እያነበቡ ወደ ሙዝደሊፋ ጉዞ ይጀምራሉ። እዛ በደረሱ ጊዜ የመግሪብ እና የኢሻ ሶላት አጣምረው የሚሰግዱ ሲሆን የኢሻን ሁለት ረከአዎች ያሳጥራሉ።

ምሽቱን ሙዝደሊፋ ላይ ያሳልፋሉ፤ የፈጅርንም ሶላት እዛው ይሰግዳሉ። በ10ኛው ዙልሂጃ ፀሐይዋ ከመውጣቷ በፊት በአቀባ ምሰሶዎች ላይ የሚወረውሩትን ሰባት ጠጠሮች ጠዋት ማለዳ በመልቀም ወደ ሚና ያቀናሉ።

አንድ ሰው ይህን ከረሳ ወይም በሌላ ምክኒያት ለምሳሌ ከሙዝደሊፋ ጠጠር ሊያገኝ ካልቻለ የሽንብራ ፍሬ መጠን ያህል ያላቸውን ጠጠሮች ሚና ውስጥ ማንሳት ይችላል።

ሐጅ ፣ ጦልቢያ እና አረፋ ተመልከቱ

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share