አስማኡሏሁል ሁስና የአሏህ ስም እና ባህሪያት

Author picture
የአሏህ ስሞች በተመለከተ አሏህ ውብ እና ፍፁም እንከን የሌለባቸው ስምና ባህሪያቶች አሉት። ስሞቹ የሚገልፁት ታላቅነቱን ፣ ልቅናውን ፣ ቅዱስነቱን እና የባህሪያቶቹን ፍፁምነት ነው።
የአሏህ ስሞች

የአሏህ ስሞች በተመለከተ አሏህ ውብ እና ፍፁም እንከን የሌለባቸው ስምና ባህሪያቶች አሉት። ስሞቹ የሚገልፁት ታላቅነቱን ፣ ልቅናውን ፣ ቅዱስነቱን እና የባህሪያቶቹን ፍፁምነት ነው። አሏህ ለእራሱ አፅድቋቸዋል፤ በእነሱም እንድንጠራው (እንድንለምነው) አዞናል። ቁርአን እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 7፡180)

“ለአሏህ በጣም ውብ ስሞች አሉት፤ በእነሱም ጥሩት (ለምኑት)”

 አስማኡሏሁል ሁስና የአሏህ ስሞች

አንድ ሙስሊም በሁሉም የአሏህ ስሞች ማመን እና ትርጉማቸውን ሳይቀይር ፣ ሳይክድ ፣ ከፍጡራኖቹ ጋር ሳያመሳስል ማፅደቅ አለበት። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሹራ 42፡11)

“እሱን የሚመስል ምንም ነገር የለም። እሱ ሁሉን ሰሚ ፣ ሁሉን ተመልካች ነው።”

አንዳንዶቹ የአሏህ ስሞች አረህማን (በጣም ርህሩህ) ፣ አረሂም (በጣም አዛኝ) ፣ አል-ሐሊቅ (ፈጣሪው) ፣ አል-መሊክ (ንጉሱ) ፣ አል-ቁዱስ (ቅዱሱ) ፣ አል-አዚዝ (አሸናፊው) ፣ አል-ሐኪም (ዳኛው) ፣ አሰላም (የሰላም ምንጭ) ፣ አል-አሊም (ሁሉን አዋቂ) የሚሉት ናቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“አሏህ ዘጠና ዘጠኝ ስሞች አሉት። አንድ መቶ ሲቀነስ አንድ። በትርጉማቸው ያመነ ሰው (በሚያመላክቱትም ነገር የሰራባቸው) ጀነት ይገባል።”

አሏህ የሚለውን ርዕስ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share