ሶሃባ ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ሰሃቢ ደግሞ ነጠላ ቁጥር አመልካች ነው። ሶሃባ ማለት ነብዩ ሙሐመድ የሚያውቁ ፣ ያዩ ፣ በአስተምህሮታቸው የሚያምኑ እና ሙስሊሞች ሆነው የሞቱ ሃዋሪያዎቹ ናቸው።
ሶሃባ

ሶሃባ ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ሰሃቢ ደግሞ ነጠላ ቁጥር አመልካች ነው። ሶሃባዎች ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የሚያውቁ ፣ ያዩ ፣ በአስተምህሮታቸው የሚያምኑ እና ሙስሊሞች ሆነው የሞቱ ሃዋሪያዎቹ ናቸው። በእርግጥ የሙስሊሙ ምርጥ ትውልድ ብርቅየ ምሳሌዎች ናቸው።

ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በቀጥታ ትዕዛዛትን ተቀብለዋል፤ ምሳሌውን ተከትለዋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“ከተከታዮቼ ምርጦቹ በእኔ ክፍለ ዘመን ያሉ ትውልዶች ናቸው። ከዚያም ከእነሱ ቡኋላ የመጡ እና ከቡኋለኞቹም ቀጥለው የመጡት ናቸው።”

ሶሃባ

መካ ከተማ ድል ካደረጉ እስልምናን ከተቀበሉት በተጨማሪ ሶሃቦች ሙሐጅሮች እና አንሷሮች ጨምሮ ይይዛል።

  1. ሙሐጅሩን (ስደተኞቹ) በመጀመሪያው የእስልምና ተልዕኮ እስልምናን የተቀበሉና ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ድጋፍ ያደረጉ ከዛ ቡኋላም አሏህ ከመካ ወደ መዲና ከተማ እንዲሰደዱ በፈቀደላቸው ጊዜ አብረዋቸው የተሰደዱት ናቸው።
  2. አንሷር (ረዳቶቹ) በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሚያምኑት ፣ መጠለያ የሰጡት እና የረዱት የመዲና ነዋሪዎች ናቸው።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና መሰደዳቸው

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና መሰደዳቸውን ተከትሎ መስጅዱን ካሰፉ በኋላ የሰሩት ሁለተኛው ትልወቁ ስራ የሙሐጅሮች እና የአንሷሮችን ወንድማማችነት ትስስር ማጠናከር ነበር።

ስለ ሙሐጅሮች አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐሽር 59፡8)

“ለእነአዚያ የአሏህን ችሮታ እና ውዴታ ፈልገው ቤታቸውን እና ንብረታቸውን ትተው የወጡ ፣ አሏህን እና መልዕክተኛውን የረዱ ድሃ ስደተኞች፤ በእርግጥ እነሱ እውነተኞቹ ናቸው።”

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)  አንሷሮችን ሲያናግሩ እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ! እናንተ ለእኔ በጣም ተወዳጅ ህዝቦች ናችሁ።” ይህንኑ ሁለት ጊዜ ደግመው አሉ።

እያንዳዱ ሙስሊም ለነብዩ ሶሃባዎች ትልቅ አክብሮት መስጠት እና አርአያው አድርጎ መያዝ አለበት።

እያንዳዱ ሙስሊም ለነብዩ ሶሃባዎች ትልቅ አክብሮት መስጠት እና አርአያው አድርጎ መያዝ አለበት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“ሶሃባዎቼን እንዳትሰድቡ (እንዳትጎዱ)፤ (ለአሏህ ብላችሁ) የእሁድን ተራራ የሚያክል ወርቅ ብትሰጡ እንኳ ከሙድ ፣ (የአንድ ኪሎ ግራም ሁለት ሶስተኛ) ጋር እኩል አይሆንም። አንዳቸው እንኳ ከሰጡት ግማሽ ሙድ ጋር እኩል አይሆንም” ብለዋል።

አሏህ ስለእነሱ ሲናገር እንዲህ ብሏል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፈትህ 48፡29)

“ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ ነው። እነዚያ እሱ ጋር ያሉት በከሃዲዎች ላይ ሃይለኞች፤ በመካከላቸው አዛኞች ናቸው። ከአሏህ ችሮታን እና ውዴታን ፈልገው አጎንባሾች እና ሰጋጆች ሆነው ታያቸዋለህ። ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ በፊታቸው ላይ ናት። ያ በተውራት ውስጥ የተገለፀበት ነው። ነገርግን በኢንጅሉም ውስጥ ምሳሌዎች ቀንዘሉን እንዳወጣ አዝመራና ቀንዘሉን እንዳበረታው  ፣ እንደወፈረና ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ሆኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ አዝመራ ነው። (ያበረታቸው እና ያበዛቸው) ከሃዲዎችን በእነሱ ሊያስቆጭ ነው። አሏህም እነዚያ ያመኑትን እና መልካም የሰሩትን ምህረትን እና ታላቅ ምንዳ ቃል ገብቶላቸዋል።”

ሰሃቢያት የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ነጠላ ቁጥር አመልካቹ ደግሞ ሰሃቢያ የሚው ነው። ሰሃቢያት ማለት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሴት ሃዋሪያዎች ማለት ነው።

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share