በምድር ላይ ተንቀሳቀሱ በላቸው

Author picture
በምድር ላይ ተንቀሳቀሱ! ይህ በምድር ላይ ተንቀሳቀሱ የተሰኘ ጽሑፍ ተፈጥሮ እንዴት ህሊናን እንደምታድስ እና ጭንቀትን እንደምታስወግድ ያስረዳል። ከቤትዎ ወጥተው የተፈጥሮን ውበት በመቃኘት እና ዓለምን በመጎብኘት ህይወትዎን ያድሱ!

ህሊናን ከሚያሳርፉ እና የጭንቀትና የሐሳብ ደመናን ከሚበታትኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ በተለያዩ ሀገራት መዟዟር ፣ ጋራ ሸንተረሮችን ማቋረጥ ፣ በሰፊዋ ምድር ላይ መሄድና ከተገለፀው የፍጥረተ-ዓለም መጽሐፍት ላይ እየተመለከቱ የአምላክነትን ብዕር በህዋው ገፆች ላይ ውብ አንቀፆችን ሲፅፉ ማየት ፣ ደስታን የሚፈጥሩ ድንቅ መናፈሻዎችን ፣ አፀዶችን እና የተጠላለፉ አትክልታማ ስፍራዎችን መቃኘት ነው።

ከቤትህ ውጣ ፣ በዙሪያህ ያሉትን ተመልከት ፣ ከፊትና ከኋላህ ያሉትንም ቃኝ፤ ተራራ ላይ ውጣ ፣ ሸለቆዎች ውስጥ ውረድ፤ ዛፎች ላይም ውጣ ፣ ንፁህ ውሃ ተጎንጭ አፍንጫህን አበቦች ላይ አሳርፈህ በሚያውደው መዓዛቸው ነፍስህን አሳርፋት፤ የዚያኔ ነፍስህን እንደዘማሪ ወፍ ነፃነት ተሰምቷት በደስታ ህዋ ላይ ስትንሳፈፍ ታገኛታለህ።

ከቤትህ ውጣ ጥቁሩን ግርዶ ከዓይንህ አስወግድ ከዚያም አሏህ በፈጠራቸው ሰፋፊዎቹ ጎዳናዎች ላይ እያደስከውና እያጠራኸው ሂድ።

ስራ ፈቶ ጠባብ ክፍል ውስጥ መሸጎጥ ራስን ለማጥፋት ቀላልና ውጤታማ መነገድ ነው። ዓለም ማለት ያቺ ትንሿ ክፍልህ አይደለችም። አንተም ሁሉም ሰዎች አይደለህም ታዲያ ለሃዘን ወታደሮች እጅህን መስጠት ለምን አስፈለገ።

ንቃ! በዓይንህ በጆሮህና በልብህ ቀላሎችም ከባዶችም ሆናችሁ ተንቀሳቀሱ ብለህ ለልብ… በሃይቆች መካከልና የፍቅር ዲስኩሮችን በሚተርኩ ዘማሪ አዕዋፋት መካከል ሆነህ እንዲሁም ከኮረብታው ላይ ጀምሮ የነበረውን ጉዞውን በሚተርከው ወራጅ ውሃ መካከል ሆነህ ቅዱስ ቁርአን ለማንበብ ተነሳ።

ጭንቀት ለሚሰማቸው ሰዎችና ጠባቧ ክፍላቸው ለጨለመችባቸው ሰዎች ሃኪሞች የሚሠጡት ምክር በምድር ላይ እንዲንሸራሸሩ ነው። ታዲያ አሁኑኑ ተነሳ! አብሽር ተጓዝ። እንደሰት እናስተንትን ፣ እናስብ።

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share