በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለ ገደብ

Author picture
በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለ ገደብ ብሚለው ትምህርት ውስጥ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ሊኖራቸው ስለሚገባ የግኑኝነት ደንቦች ትማራላችሁ።

በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለ ገደብ ብሚለው ትምህርት ውስጥ በአንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት መካከል ሊኖራቸው ስለሚገባ የግኑኝነት ደንቦች ትማራላችሁ።

የጽሁፉ አላማ

  1. በወንድ እና በሴት መካከል ሊኖር የሚገባው የግኑኝነት አደብ የሚቆጣጠረውን የሸሪአ የህግ ማዕቀፍ ጠቀሜታ ታውቃላችሁ።
  2. አንድ ወንድ እና በአንዲት ሴት ቅርርብ ውስጥ የተደረጉ ገደቦችን ታውቃላችሁ።

የእስልምና ህግ በወንዶች እና በሴቶች መካከል ያለውን ቅርርብ ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች የሰዎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ይሰጣል።

አሏህ ወንዶችን እና ሴቶችን የፈጠረው እርስ በእርሳቸው እንዲፈላለጉ እና እንዲሳሳቡ አድርጎ ነው። የዚህ ስበት እና መፈላለግ ውጤት ህጋዊ የሚሆነው በጋብቻ ብቻ ነው። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 5096 ፣ ሙስሊም 2741)

‹‹ከእኔ በኋላ ለወንዶች ከሴቶች የበለጠ የከፋ ፈተናን አልተውኩም።››

በወንድ እና በሴት መካከል ባለው ቅርርብ በጣም የከፋው እና አደገኛው ነገር ዝሙት ላይ መውደቅ ነው።

ሸሪአ ይህን ስርአት ማጣት እና ግብረገብነት የጎደለው ተግባር መከላከል ብቻ ሳይሆን ወደ እሱ መቅረብንም በጥብቅ ከልክሏል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኢስራዕ 32)

“ዝሙትን አትቅረቡ። እሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነውና። መንገድነቱም ከፋ!”

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 6243 ፣ ሙስሊም 2657)

‹‹የአይን ዝሙት (የተከለከለን ነገር) ማየቱ ነው። የምላስ ዝሙት ማውራቱ ነው። እንዲሁም የውስጥ ፍላጎት እና ምኞቶች ናቸው። ሀፍረተ ገላዎች ይህን ሁሉ ይመሰክራሉ ወይም ይክዳሉ።››

ማንኛውንም ስህተት እና ጥመት ለማስቀረት ሲባል እና መጥፎ ውጤት ከማስከተሉ በፊት በሴቶች እና በወንዶች ቅርርብ ላይ አስፈላጊ ሸሪአዊ ቁጥጥሮችን እና ገደቦችን አስቀምጧል።

ለምሳሌ መግዛት ፣ መሸጥ እና ሌሎች የተፈቀዱ ግብይቶች እንዲሁም የግድ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ሴት ዶክተሮች በማይኖሩበት ጊዜ አንዲትን ሴት ማከም ወ.ዘ.ተ ናቸው። ከእነዚህ ቁጥጥሮች እና ገደቦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-

እይታን መስበር

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 30-31)

“(30) ለምዕመናን ንገራቸው! ዓይኖቻቸውን ያልተፈቀደን ከማየት ይከልከሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለእነሱ የተሻለ ነው። አሏህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው። (31) ለምዕመናትም ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ።”

መነካካትን ወይም በእጅ መጨባበጥን ማስወገድ

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡ መልዕክተኛውን የአብሮነት ቃልኪዳን ለሴቶች ገለፃ በተመለከተ ከተናገሩ በኋላ በአሏህ ይሁንብኝ የአሏህ መልዕክተኛ እጅ የአንዲትን ሴት እጅ ነክቶ አያውቅም።›› (ቡኻሪ 5288 ፣ ሙስሊም 1866)

መቂል ቢን ያስር እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹አንድ ሰው ያልተፈቀደችለትን ሴት ከሚነካ የብረት ድዥኖ በአናቱ ቢገባ ይሻለዋል።›› (አጦበራኒ፡ አል-ሙጀም አል-ኪበር 486፤ አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)

ሴት ጋር ብቻውን ተገልሎ መቀመጥ

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 5233 ፣ ሙስሊም 1341)

‹‹ከመህረሙ ጋር ካልሆነ በቀር አንድም ወንድ ከሴት ጋር ብቻውን መሆን የለበትም።››

እንዲህም ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አህመድ 115)

‹‹አንዳችሁም ከሴት ጋር ብቻውን አይሆንም ሶስተኛው ሸይጧን ቢሆን እንጅ።››

በሴቶች ላይ የተጣሉ ገደቦች

ሙስሊም ሴቶች ከወንዶች ጋር የግድ መቀራረብ በሚያስፈልግበት ጊዜ ሊከተሏቸው እና ሊጠብቋቸው የሚገቡ ደንቦች እና ድንበሮች አሉ።

ህጋዊ የሸሪአ የአለባበስ ስርአትን መከተል

ሙስሊም ሴት በመጀመሪያ የአሏህን ትዕዛዝ በማክበር እና ከዚያም ወንዶች እንዲያከብሯት እና በንግግራቸው ፣ በድርጊታቸው እና በእይታቸው እንዳይጎዷት ህጋዊ የሸሪአ የአለባበስ ስርአትን መከተል አለባት። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 31)

“ለምዕመናትም ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ።”

አሏህ እንዲህም ብሏል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ አህዛብ 59)

“አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ ፣ ለሴት ልጆችህም ፣ ለምዕናን ሚስቶችም መከናነቢያቸውን በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁ እና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው። አሏህ መሃሪ አዛኝ ነው።”

ወንዶች በሚኖሩ ጊዜ ሽቶ አለመነስነስ

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ነሳኢ 5126)

“ሰዎች ጠረኗን ያሸቱ ዘንድ ሽቶ ነስንሳ በሰዎች በኩል የምታልፍ ሴት ዝሙተኛ ናት አሉ።”

ሳይቅለሰለሱ ቆፍጠን ብሎ መናገር

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህዛብ 32)

“የነብዩ ሴቶች ሆይ! ከሴቶች እንደማናቸውም አይደላችሁም። አሏህን ብትፈሩ ትበልጣላችሁ። ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጀል በንግግር አትለስልሱ። መልካም ንግግርንም ተናገሩ።”

በጨዋነት እና በይሉኝታ (በሃያዕ) መራመድ

የሹአይብ ሴት ልጅ የአባቷን መልዕክት ለነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ)  ልታደርስ በሄደች ጊዜ የነበረውን ሁኔታ አሏህ ስለ እሷ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ቀሶስ 25)

“ከሁለቱ አንደኛይቱ ከሃፍረት ጋር የምትሄድ ሆና መጣች።”

አሏህ ስለሴቶች ሲናገር እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 31)

ከጌጦቻቸው የደበቁት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ።

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለ ገደብ

‹‹በሁለቱ ፆታዎች መካከል ያለ ገደብ›› የሚለው ትምህርት ፈተና 5 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 4 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 5

Bookmark question icon

1 ትክክለኛ መልሶችን ምረጥ፡ መህረም ያልሆነች ሴት ጋር ለብቻው ተገልሎ መቀመጥ አይፈቀድም። ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት በአንዳቸው ሁኔታ ካልሆነ በቀር

2 / 5

Bookmark question icon

2 ‹‹ዝሙትን አትቅረቡ። እሱ በእርግጥ መጥፎ ስራ ነው። ምንገድነቱም ከፋ።›› (ኢስራዕ 32) ይህ የአሏህ ንግግር የሚያመላክተው ምንድን ነው?

3 / 5

Bookmark question icon

3 እይታን መስበር ወይም ዝቅ ማድረግ ለወንድ ልጅ ግዴታ ሲሆን ለሴት ልጅ ግን ግዴታ አይደለም።

4 / 5

Bookmark question icon

4 ሴት ልጅ በሸሪአ የተፈቀደ የአለባበስ ስርአትን መከተል ከሚያስገኛቸው ጥቅሞች መካከል

5 / 5

Bookmark question icon

5 ሴት ልጅ መህረም ካልሆኑ ወንዶች ጋር መቀላቀል ወይም መቀራረብ ከሚፈቀድበት በቂ ምክኒያቶች መካከል የሆነው የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »
ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

ወሲባዊ ግንኙነት በእስልምና እይታ

እስልምና ወሲባዊ ግንኙነት ሊታፈን የማይገባው እንደሆነና በተገቢው መንገድ ሊረካ የሚገባ አስፈላጊ የሰው ልጅ ፍላጎት እንደሆነ ያስተምራል። ወሲባዊ ግንኙነት እንደ ቀላል ነገር የሚታይ  አይደለም፤ እንዲሁም አንድ

Read More »

የልጆች መብት በእስልምና

የልጆች መብት በእስልምና በሚለው ትምህርት ውስጥ ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን መብት ትማራላችሁ። ልጆችን በማሳደግ ዙሪያ ከሸሪአ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ ነገሮችን ታውቃላችሁ።

Read More »

የጋብቻ ጥያቄ አደቦች (ስነ-ስርአቶች)

በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ጋብቻ ጥያቄ ፅንሰ ሃሳብ እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ስነ-ስርአቶችን ትማራላችሁ። በእስልምና ውስጥ የጋብቻ ጥያቄን ሲያቀርቡ ሊከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share