ተየሙም ማለት እራስን ለሶላት ለማዘጋጀት በማሰብ በውሃ ፈንታ በንፁህ አሸዋ ወይም አፈር ፊትን እና እጅን በማበስ የሚፈፀም ደረቅ ውዱእ (ትጥበት) ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(አል-ቁርአን 4፡43)
ውሃ ባታገኙ፤ ንፁህ በሆነ የምድር ገፅ ተየሙም አድርጉ። ፊቶቻችሁን እና እጆቻችሁን (በእሱ) አብሱ። አሏህ ይቅር ባይ መሃሪ ነውና።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(አህመድ)
“ምድር በሙሉ ለእኔ እና ለተከታዮቼ ንፁህ የመስገጃ ቦታ ተደረገችልን። ከተከታዮቼ መስገድ ፈልጎ ውሃ ሊያገኝ ያልቻለ ሰው ለመፅዳጃ እና ለመስገጃ የሚሆን አፈር ያገኛል።”

ውዱእ ለማድረግ ውሃ ሊያገን የማይችል ሰው ወይም ቢያገኝም ለመጠጥ ትሆነኛለች ብሎ ያሰበ ሰው ወይም ደግሞ ውሃውን ብጠቀም ህይወቴን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሎ ከፈራ ወይም ደግሞ ብጠቀም ህመም ያስከትልብኛል እና ህመሙ ስር እንዲሰድ ያደርግብኛል ብሎ ከፈራ ተየሙም ማድረግ ይኖርበታል።
ተየሙም የሚደረገው ቢስሚላህ በማለት በእጆች አፈሩን መታ መታ በማድረግ ፊትን እና እጆችን እስከ አንጓ ድረስ አንድ ጊዜ በማበስ ነው።
የቀኝ እጅን ጀርባ (አይበሉባ) በግራ እጅ መዳፍ ማበስ። ከዛም የግራ እጅን ጀርባ (አይበሉባ) በቀኝ እጅ መዳፍ ማበስ ነው።
ውዱእ የሚያስፈታ ነገር ሁሉ ተየሙምን ያስፈታል። ተየሙም አድርገው ከሰገዱ በኋላ ውሃ ቢያገኙ ሶላቱን መድገም አያስፈልግም።
ውዱእ ፣ የገላ ትጥበት እና ንፅህና ተመልከቱ




Share