እስልምና የንፅህና ሃይማኖት ነው። በእርግጥ ንፅህና በእስልምና ሃይማኖት የእምነቱ አንድ አካል ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊሞች የግል ንፅህናቸውን የሚጠብቁባቸውን መንገዶች ሁሉ አሳይተዋል።
የሽንት ቤት አጠቃቀም ስነምግባር ሳይቀር ማለት ነው። ንፅህናችነን ከምንጠብቅባቸው መንገዶች አንዱ እስቲንጃ ተብሎ ይጠራል።

እስቲንጃ ለተፈጥሮ ጥሪ ምላሽ ከሰጡ ቡኋላ ውሃ በመጠቀም እራስን ከቆሻሻ የሚያጸዱበት ተግባር ነው። ውሃ ከሌለ የሽንት ቤት ወረቀት ወይም ድንጋይ ለዚህ አላማ ያገለግላሉ።
ኢስቲጅማር የሚለው ቃል በድንጋይ ወይም በደረቅ አፈር ወይም በወረቀት አፍረተገላን የማፅዳዳት ተግባርን የሚገልፅ ነው።
የሽንት ቤት አጠቃቀም መመሪያ


- አንድ ሰው ወደ ሽንት ቤት ከመግባቱ በፊት ቢስሚላህ አሏሁመ ኢኒ አኡዙቢከ ሚነል ሁቡሲ ወል ኸባኢስ (በአሏህ ስም፡ አልህ ሆይ! ከሴትና ከወንድ ሰይጣናት ተንኮል በአንተ እጠበቃለሁ) ማለት አለበት። በማስከተልም የግራ እግሩን በማስቀደም ወደ ሽንትቤቱ ይገባል።
- ከሽንት ቤት ሲወጣ የቀኝ እግሩን በማስቀደም ነው። እንደወጣም ኡፍራነከ (ምህረትህን እሻለሁ) ማለት አለበት።
- የአሏህ ስም ያለበት ማንኛውም ነገር ይዞ መግባት አይፈቀድም።
- ሲፅዳዱ ፊትን ወይም ጀርባን ወደ ቂብላ ማዞር አይፈቀድም
- መሸፈን ያለበት የአካል ክፍል (ሃፍረተ ገላ) መሸፈን አለበት። የወንድ ልጅ አውራ (ሃፍረተ ገላ) ከእንብርቱ እስከ ጉልበቱ መካከል ያለው ነው። እንብርቱን እና ጉልበቱን ጨምሮ ማለት ነው። የሴት ልጅ አውራ (ሃፍረተ ገላ) ሙሉ አካሏ ነው።

- ልብሱን ወይም አካሉን ሽንት ወይም አይነምድር ያልነካው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት።
- ሃፍረተ ስጋውን በውሃ ማፅዳት አለበት። ውሃ ከለለ በሽንትቤት ወረቀት ወይም በድንጋይ ወይም ደግሞ ለዚህ አላማ ተስማሚ በሆነ ማንኛውም ነገር ሊያፀዳ ይችላል። የሽንት ቤት ወረቀት እና ውሃ አጣምሮ የሚጠቀም ከሆነ የሽንትቤት ወረቀቱን መጀመሪያ ተጠቅሞ በመቀጠል ውሃ መጠቀም ይኖርበታል። ለበለጠ ንፅህና በላጩ ይሄ ነው።
- ለማፅዳት ግራ እጅን መጠቀም ተገቢ ነው።
ጦሃራን ተመልከቱ




Share