ኩፍር የሚለው የአረንኛ ቃል “መሸሸግ ፣ መደበቅ ወይም መሸፈን” የሚል ትርጉም አለው። ኩፍር የኢማን ተቃራኒ ሲሆን እውነትን መሸሸግ ወይም መደበቅ ነው። በእስልምና ህግ መሰረት በአሏህ እና በመልዕክተኛ አለማመን ማለት ነው።

በእርግጥ አሏህ እንድናምን ባዘዘን ነገር ላይ መለኮታዊ አስተምህሮቱ ደርሶት በቃል መካዱን ሳይናገር በልቡ ያልተቀበለ ወይም በቀልቡ መካድን የተናገረ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ያደረገ ሰው የኩፍር ባህሪ ያለው ሰው ነው።
በቁርአን እና በሱና ከእምነት እንደሚያስወጣ የተገለፀን ተግባር የፈፀመ ሰው ወይም እንዲህ አይነት ባህሪ ያለው ሰው ካፊር (ከሃዲ) ይባላል። የዚህ ቃል ብዙ ቁጥር አመልካች ኩፍር የሚለው ቃል ነው።
ሁለት የኩፍር ደረጃዎች አሉ።
ኩፍር አል-አክበር (ትልቁ ክህደት)፡
ይህ ጉዳይ ከእስልምና ሃይማኖት ሙሉ በሙሉ የሚያስወጣ ሲሆን አምስት አይነቶች አሉት

ሀ) መለኮታዊ እውነታን መካድ
ለ) ልክ እንደ ኢብሊስ ለመለኮታዊ እውነታ እውቅና ቢቸሩም እንኳ በእብሪተኝነት መጥመም
ሐ) ከኢማን ምሰሶዎች ውስጥ አንዱን ወይም ሁሉንም መጠራጠር ወይም መካድ
መ) ሆንብሎ ከመለኮታዊ እውነታ መጥመም
ሰ) የንፍቅና ክህደት፡ ይህ ማለት ከሙዕሚኖች ጋር ሲሆን ክህደትን መደበቅ እና ሙስሊሞችን ለማታለል ኢማምን መግለጥ ነው።
አል-ኩፍር አል-አስገር (ትንሹ ክህደት)
ይህንን የክህደት ተግባር የሚፈፅም ሰው ከኢስላም አያስወጣውም ነገርግን ኢማኑ ወይም እምነቱ ጎደሎ ነው።
ከትንሹ የክህደት አይነት ውስጥ አንዱ የሆነው ኩፍሩን ኒእማ ተብሎ የሚጠራው ነው። ይህ የአሏህ ችሮታዎችን ወይም ውለታዎችን ባለማመስገን የሚገለፅ ክህደት ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ነህል 16፡112)
ደህንነቷ የተጠበቀ እና የረካች፤ ሲሳይ ከሁሉም ቦታ ወደ እሷ የሚመጣላት የሆነችን ከተማ (መካ) አሏህ ምሳሌ አደረገ። ነገርግን የአሏህን ችሮታ ካደች (ህዝቦቿ)። እናም ይሰሩት በነበረው ሃጢያት አሏህ ረሃብና ፍርሃትን እንድትቀምስ አደረጋት።
የዚህ ኩፍር አይነት ሌላው መገለጫ ሙስሊምን መዋጋት ወይም መፋለም ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“አንድን ሙስሊም መጉዳት (ማጎሳቆል) ጭካኔ ነው፤ እሱን መፋለም (መዋጋት) ደግሞ ክህደት ነው።”


Share