ቅዱስ ቁርአን የሃያሉ አሏህ ቃል ነው። እሱን የሚያነብ ሰው ህግጋቶቹን እና ሊከተላቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ማወቅ አለበት። በዚህ ትምህርት እነዚህን ህግጋቶች እና ስነ-ስርአቶች ትማራላችሁ።
የጽሁፉ አላማ
ቅዱስ ቁርአን የማንበብ ስንቆች እና አደቦች (ስነ-ስርአቶች) ትማራላችሁ።
ቁርአንን የመሐፈዝ (የመሸምደድ) ህግጋት
1 ሙሉ ቁርአንን በቃል መሐፈዝ (መሸምደድ) በሁሉም ህዝብ ላይ የሚጠበቅ የጋራ ግዴታ ነው።
2 ከቁርአን ለሶላት የሚያስፈልገውን ነገር መሸምደድ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ይህም ሱረቱል ፋቲሃ ነው።
3 ከቁርአን የገራለትን መሸምደድ ለሙስሊም ሰው የተወደደ ነው። ቁርአንን መሸምደድ ትልቅ ትሩፋት እና ትልቅ ሽልማት አለውና። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ 4937)
‹‹ቁርአንን የሚያነብ እና የሚሸመድድ ሰው ምስያው ልክ እንደ ተከበሩ እና ፃድቅ ሁጃጆች ነው።››
ቁርአን የመቅራት (የማንበብ) ህግጋት
ቁርአንን ማንበብ እና እስከቻለው ድረስ ማድረግ ለሙስሊም ሰው የተወደደ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ፋጢር 29)
“በእርግጥ! በእነዚያ የአሏህን መጽሐፍ የሚያነቡ ፣ ሶላትንም አስተካክለው የሚሰግዱ ፣ ከሰጠናቸውም ሲሳይ በሚስጥርም ሆነ በግልፅ የሚለግሱ በፍፁም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ።”
የቁርአን ንባብን ማድመጥ እና ትኩረት መስጠት
ቁርአን ሲነበብ ሲሰሙ ማድመጥ እና ለእሱ ትኩረት መስጠት በሙስሊም ሰው ላይ ግዴታ ነው። በተለይ ደግሞ ሶላት እና በጁምአ ሁጥባ (ትምህርት) ውስጥ ሲሆን ማለት ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አዕራፍ 204)
“ቁርአን በተነበበ ጊዜ እሱን አድምጡ። ፀጥም በሉ ይታዘንላችኋልና።”
ቁርአን በሌሎች ቦታዎች ላይ (ከሶላት እና ከጁምአ ሁጥባ ውጭ) በሚነበብ ጊዜ እሱን ማድመጥ እና ለእነሱ ትኩረት መስጠት የተወደደ ነው። ምክኒያቱም ለሃያሉ አሏህ ቃል ያለንን አክብሮት እና ትህትና መሳያ ስለሆነ ነው።
በቅዱስ ቁርአን የመስራት ሸሪአዊ ብያኔ
ሁሉም ሰው በቁርአን ማመን እና ህግጋቱን ማጥናት ፣ የተከለከሉትን መከልከል ፣ የታዘዙትን መታዘዝ እና በህግጋቱ መሰረት መስራት አለበት። ሃያሉ አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 121)
“እነዚያ መጽሐፉን የሰጠናቸው ተገቢ ንባብን ያነባሉ።
ኢብን አባስ እና ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹የተፈቀደውን ይፈቅዳል፤ የተከለከለውንም ይከለክላሉ። ከተከለከለውም ነገር አንድንም ነገር አይቀይሩም።›› (ተፍሲር ኢብን ከሲር 1/403)
አቡዱሏህ ቢን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አስር አንቀፆችን የምንማር ከሆነ በውስጡ ያለውን ነገር እስከምናውቅ ድረስ ከዚያ በኋላ የተገለጡትን (ራዕይ) እንማርም ነበር።›› (አል-ሐኪም 2047) ‹‹በውስጡ ያለውን ነገር›› የሚለው ንግግር ከሐዲስ ዘጋቢዎች አንዱ እንዳብራራው በውስጡ ሊተግባር ወይም ሊሰራበት የሚችል ስራን ማለቱ ነው።
ቁርአንን በማንበብ መፅናት እና እሱን አለመተው
አንድ ሙስሊም ሰው ቁርአንን በማንበብ ላይ ለመፅናት ቃል መግባት አለበት። አንዲትም ቀን ከቁርአን የሆነ ነገር ሳያነብ ማሳለፍ የለበትም። እንዳይረሳው ወይም ደግሞ እንዳይተወው መጠንቀቅ አለበት። አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ፉርቃን 30)
“መልዕክተኛውም ጌታየ ሆይ! ህዝቦቼ ይህን ቁርአን የተተወ ነገር አድርገው ያዙት አለ።”
አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይዞ እንዳወራው እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ 5033)
‹‹ቁርአንን በማንበብ ላይ ፅና። ነፍሴ በእጁ በሆነው ይሁንብኝ፡ ከማሰሪያ ገመዷ ከተለቀቀች ግመል የበለጠ ቁርአን ይሸሻል (ይረሳልና) አሉ።››
ቅዱስ ቁርአንን የማንበብ ስነ-ስርአት
ቁርአንን ማንበብ ተቀባይነት እና ሽልማት ያለው እንዲሆን ልንከተላቸው የሚገቡ ስነ-ስርአተቶች አሉ። እነዚህ ስነ-ስርአቶች (አደቦች) ቁርአንን ከማንበባችን በፊት እና በምናነብበት ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ ናቸው።
ቅዱስ ቁርአን ከማንበባችን በፊት ልንከተላቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶች
1 የአሏህን ውዴታ እና ሽልማት እንደምናገኝበት አስበን በኢህላስ (በቅንነት) ማንበብ ይኖርብናል። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በይና 5)
ሃይማኖትን ለእሱ ያጠሩ ሲሆኑ አሏህን ሊገዙ እንጅ አልታዘዙም።
ይህ አደብ ቁርአን ከመቅራት በፊት የምንከተለው ቢሆንም በምናነብበት ጊዜም ይቀጥላላል።
2 ከትልቁ እና ከትንሹ ሐደስ (የንፅህና ጉድለት) የተጥራራን (የነፃን) መሆን አለብን። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ዋቂአ 79)
ሙጧሃሩን (የተጥራሩ) እንጅ አይነኩትም።
3 የቁርአን መንገድ ነውና አፍን ማፅዳት ያስፈልጋል። ሁዘይፋ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ “ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማታ ለተሃጁድ በተነሱ ጊዜ አፋቸውን በሲዋክ ይቦርሹ ነበር።” (ቡኻሪ 1136 ፣ ሙስሊም 255)
4 ሲያነቡ ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዞር ያስፈልጋል። ምክኒያቱም ይህ አቅጣጫ በጣም የተከበረ እና የላቀ ነውና። በአል-ሚራዊ ውስጥ እንደሰፈረው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል አለ አቡ ሁረይራ፡ ‹‹ሁሉም ነገር ሰብሳቢ አለው። የሰብሳቢዎች ሁሉ ሰብሳቢ ደግሞ ወደ ቂብላ አቅጣጫ መዞር ነው አሉ።›› (በጦበራኒ ተዘግቧል 2354) ሰነዱ ሐሰን ነው (ጥሩ የዘገባ ሰንሰለት አለው)።
5 ሃያሉ አሏህ እንዳለው የእሱን ጥበቃ መሻት (መፈለግ)፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ነህል 98)
“ቁርአን በምታነብ ጊዜ ከተረገመው ሰይጣን በአሏህ ተጠበቅ።”
6 አነስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ‹‹አንድ ቀን ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከእኛ ጋር ሆነው እያለ እንቅልፍ ወሰዳቸው። ከዛም ፈገግ ብለው ከራሳቸው ቀጥ አሉ። እኛም፡ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ምንድን ነው የሚያስቅሁ? አልናቸው። እሳቸውም፡ ‹‹አንድ ምዕራፍ አሁን ተገለጠልኝ አሉ። ከዛም አነበቡ፡ በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። “በእርግጥ ከውሰርን (ጀነት ወንዝ) ሰጠንህ። ለጌታህም ስገድ፤ በስሙ ሰዋም። የሚጠላህ እሱ በእርግጥ ዘሩ የተቋረጠ ነው።”›› (ሱረቱል ከውሰር 1-3) (ሙስሊም 400)
ቁርአን በምናነብ ጊዜ ልንከተላቸው የሚገቡ አዳቦች (ስነ-ስርአቶች)
1 ቁርአንን ቀስ እና ረጋ ብሎ ማንበብ፡ ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሙዘሚል 4)
“ቁርአን ማንበብን በደንብ አንብብ”
2 ቁርአን በተጅዊድ ማንበብ፡ አነስ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአነባበብ ሁኔታ እንዴት እንደሆነ ተጠይቆ ሲመልስ እንዲህ አለ፡
‹‹የተወሰኑ ድምፆችን ያስረዝማሉ። ከዚያም፡ ‹‹በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው›› ያነባሉ። ሲያነቡም ‹‹በአሏህ ስም›› የሚለውን ያስረዝማሉ ፣ ‹‹እጅግ በጣምር ርህሩህ›› የሚለውን ያስረዝማሉ ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው›› የሚለውን አስረዝመው ያነባሉ። (ቡኻሪ 5046)
3 ሲያቡ ድምፅን ማሳመር፡ አል-ባር ቢን አዚዝ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(አቡዳውድ 1468)
‹‹ቁርአንን በድምፃችሁ አሳምሩ (አስውቡ)።
4 በእዝነት አንቀፅ የአሏህን እዝነት መለመን ፣ በቅጣት አንቀፅ የአሏህን ጥበቃ መፈለግ እና በውዳሴ አንቀፅ ደግሞ አሏህን ማወደስ።
ሁዘይፋ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር እየሰገደ እያለ የነበረውን ሁኔታ እንዲህ ሲል አስተላልፏል፡
“ከዚያም (ሱረቱል) ኢምራንን ጀምረው በእርጋታ መንፈስ አነበቡ። የአሏህን ልቅና የሚገልፁ አንቀፆችን ባነበቡ ጊዜ ‹ሱብሃን አሏህ› በማለት ያወድሳሉ። አሏህ መለመን የሚያወሱ አንቀፆችን ባነበቡ ጊዜ ደግሞ ‹የአሏህን ጥበቃ ይሻሉ።›” (ሙስሊም 772)
5 አንድ ሰው በሰጅደተ ቲላዋ (በግንባር መደፋት ንባብ) ባለፈ ጊዜ ሱጁድ ማድረግ የተወደደ ነው። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው እንዲህ አለች፡
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሌሊት ጊዜ ቁርአን እያነበቡ ሱጁድ ሲያደርጉ ደጋግመው ፊቴ ለፈጠራት እና በችሎታው (በጥበቡ) መስሚያዋን እና ማያዋን ለከፈለው (ጌታ) ትደፋለች ይሉ ነበር።›› (አቡዳውድ 1414)
6 ሲያነቡ በሁሹዕ መመስጥ ፣ ሰላም እና መረጋጋትን መላበስ
ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሷድ 26)
“ወደ አንተ ያወረድነው የተባረከ መጽሐፍ አንቀፆቹን እንዲያስተነትኑ እና ባለ አዕምሮዎችም እንዲገሰፁ ነው።”
Share