የወላጆች መብት በእስልምና

Author picture
በዚህ ትምህርት ውስጥ የወላጆች መብት ፣ ወላጆችን ስለ ማክበር እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ትማራላችሁ። ወላጆች በእስልምና ውስጥ ያላቸውን ደረጃ ታውቃላችሁ።

በዚህ ትምህርት ውስጥ የወላጆች መብት ፣ ወላጆችን ማክበር እና ከእሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ ነገሮችን ትማራላችሁ።

የጽሁፉ አላማ

  1. ወላጆች በእስልምና ውስጥ ያላቸውን ደረጃ ታውቃላችሁ።
  2. የወላጆች መብት ማክበር ታበረታታላችሁ፤ እነሱን አለማክበርን ታስጠነቅቃላችሁ።
  3. ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን ሃላፊነቶች እና ግዴታዎች ታውቃላችሁ።
  4. ከወላጆች ጋር በሚኖራችሁ መስተጋብር ልትከተሏቸው ሚገቡ ስነ-ስርአቶችን ታውቃላችሁ።

የወላጆች ደረጃ በእስልምና

እስልምና ለወላጆች ትልቅ ክብር አጎናፅፏቸዋል። ክብራቸው በእስልምና ውስጥ በጣም ትልቅ ከሆነው የአሏህ አሃዳዊነት ጉዳይ ጋር አስተሳስሮታል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 23)

“ጌታችሁ እሱን እንጅ ሌላን አትገዙ። ለወላጆቻችሁም መልካምን ስሩ ሲል አዘዘ።”

ሃያሉ አሏህ ወላጆችን የወንድ እና የሴት ልጆች መኖር ሰበብ አድርጓቸዋል። ልጆች ያደረጉ ቢያደርጉ የወላጆቻቸውን ሃቅ መመለስ አይችሉም።

ለልጆቻቸው ምቾት እና እንክብካቤ ሲሉ ያጋጠማቸው ፈተና ፣ ድካም እና መዛል ፣ ጉዳት ፣ እረፍት እና እንቅልፍ ማጣት እና እንግልት ሊክሱ አይችሉም።

ከአሏህ ፍትሃዊነት መገለጫዎች ውስጥ አንዱ ወላጆች ለልጆቻቸው ባደረጉላቸው ምስጉን ተግባራት እና እንክብካቤ በልጆቻቸው ላይ መብቶች ያላቸው መሆኑን መደንገጉ ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንከቡት 8)

“ሰውንም ለወላጆቹ መልካም አድራጎትን እንዲያደርግ አዘዝነው።”

እንዲህም አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሉቅማን 15)

“በቅርቢቱ አለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው።”

በሌላ በኩል ደግሞ ከሶሃቦች አንዱ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ጠየቋቸው፡ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! በጣም ላገለግለው የሚገባ ማነው? እሳቸውም፡ እናትህ አሉ። እሱም፡ ከዚያስ አላቸው። እሳቸውም እናትህ አሉት። ከዚያስ ማነው አላቸው። እሳቸውም እናትህ አሉ። እሱም ከዚያስ ማነው? አላቸው። እሳቸውም ከዚያ አባትህ አሉት።›› (ቡኻሪ 5971 ፣ ሙስሊም 2548)

ወላጆችን የማክበር ቱሩፋት

ወላጆችን ማክበር ግዴታ ነው። እነሱን ማክበር ሽልማቱ ትልቅ ነው። እርዚቅ (ሲሳይ) ወይም በረካ ለማግኘት ሰበብ ነው።

በዚህ አለም ህይወት መልካምነት ሲሆን በመጭው አለም ህይወት ደግሞ ጀነት ለመግባት ሰበብ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 2551)

‹‹ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ ፣ ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ ፣ ባፍንጫው አቧራ ውስጥ ይደፋ አሉ። የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እሱ ማን ነው? ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም፡ በእርጅና እድሜ አንዳቸውን ወይም ሁለቱንም ወላጆቹን አግኝቶ ጀነት ያልገባ ሰው ነው አሉ።››

ለወላጆች ደግ መሆን አሏህ በጣም የሚወደው ተግባር ነው። አብዱሏህ ቢን መስኡድ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጣም የሚወደደው ተግባር ምንድነው? ብሎ ጠየቃቸው። እሳቸውም፡ በወቅቱ መስገድ ነው አሉ። እሱም ከዚያስ ምንድነው? አላቸው። እሳቸውም ወላጆችን ማክበር ነው አሉ። እሱም ከዚያስ? ምንድነው አላቸው። እሳቸውም ጅሃድ ፊ ሰቢሊላህ (በአሏህ መንገድ መታገል) ነው አሉት።›› (ቡኻሪ 527 ፣ ሙስሊም 85)

ወላጆች ማክበር ከተጨማሪ ጅሃድ የበለጠ ነው። አንድ ሰው ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ኡጃሂዱ (ልታገል ፣ ጅሃድ ላድርግ) አላቸው። እሳቸውም፡ ‹‹ወላጆች አሉህን?›› አሉት።እሱም አዎ አለ። እሳቸውም፡ ‹‹ለእነሱ ጥቅም ታገል›› አሉት።›› (ቡኻሪ 5972 ፣ ሙስሊም 2549)

ወላጆችን አለማክበር

ወላጆችን አለማክበር ከትልልቅ ወንጀሎች ውስጥ አንዱ እና ከእነሱ ውስጥ ትልቁም ነው። በሐዲስ ውስጥ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 6919 ፣ ሙስሊም 87)

‹‹ከትልልቅ ወንጀሎች ሁሉትልቁ በአሏህ ላይ ማጋራት እና ወላጆችን አለማክበር ነው።››

ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸው ግዴታዎች

1 በመልካም ነገር ያያዙትን እስከቻለው ድረስ መታዘዝ አለበት። ነገርግን ያዘዙት ነገር ሃጢያት ከሆነ በዚህ ላይ መታዘዝ የለበትም።

ምክኒያቱም ፈጣሪውን አሏህን አምፆ ፍጡራኑን መታዘዝ ስለለ ነው።

2 ልጃቸውን የሚጎዱ እና የሚበድሉ ቢሆኑ እንኳ ለእነሱ ደግ መሆን አለበት። ለአሏህ ባላንጣ (ተጋሪ) እንዲያበጅ ካላዘዙት በቀር፡፡

የጀሐነም እሳት ውስጥ ዘላለም ለመኖር ጥሪ ከማድረግ የበለጠ በልጃቸው ላይ ጉዳት ሚያደርሱበት በደል አለን? አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሉቅማን 15)

“እውቀት በሌለህ ነገር በእኔ እንድትናገር ቢታገሉህ አትታተዘዛቸው። በቅርቢቱ አለም በመልካም ስራ ተወዳጃቸው።”

3 እነሱን መንከባከብ እና በቻለው መንገድ ሁሉ እነሱን መታዘዝ ፣ መውደድ እና ማገልገል አለባችሁ። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኢስራዕ 23)

“ጌታህ እሱን እንጅ ሌላን አትገዙ። ለወላጆቻችሁም መልካም ስሩ።”

4 እነሱን በማንኛውም መንገድ መጉዳት እና መበደል የለባችሁም። ‹‹ኡፍ›› ማለት ቢሆን እንኳ። በተለይ ደግሞ የእርጅና እድሜ ላይ በደረሱ ጊዜ። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 23)

“ጌታህ እንዲህ ሲል አዘዘ፡- እሱን እንጅ ሌላን አትገዙ። ለወላጆቻችሁም መልካም ስሩ። አንተ ዘንድ ሆነው የእርጅና እድሜ ላይ በደረሱ ጊዜ ኡፍ አትበላቸው።”

5 ለእነሱ ትሁት እና እራስን ዝቅ ማድረግ ያስፈልጋል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 24)

“በእዝነት የመተናነስ ክንፍን ዝቅ አድርግላቸው። ‹‹ጌታየ ሆይ! በህፃንነቴ በርህራሄ እንዳሳደጉኝ እዘንላቸውም በል።”

6 ዘወትር ምስጋናን መግለፅ እና ለውለታቸው እውቅና መስጠት ያስፈልጋል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሉቅማን 14)

“ሰውም ለወላጆቹ በጎ እንዲያደርግ በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም ላይ ሆና ወለደችው። የጡት ማስጣያ ጊዜው ሁለት አመት እድሜ ነው። ለእኔም አመስግኑ። ለወላጆቻችሁም አመስግኑ። መመለሻችሁም ወደ እኔ ነው።”

7 በደግነት ወጭያቸውን መሸፈን ያስፈልጋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 3530)

‹‹አንተ እና ገንዘብህ ለአሏህ ተገቢዎች ናችሁ። ልጆችህ በላጭ ከሆኑ ከስቦችህ መካከል ናቸው። እናም ከልጆችህ ከስብ ብላ።››

8 በህይወት እያሉ እና ከሞቱ በኋላ ለእነሱ ዱአ ማደረረግ ያስፈልጋል። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 1631)

‹‹አንድ ሰው ሲሞት ስራዎቹ ይቋረጣሉ፤ ሶስት ነገሮች ሲቀሩ። ቀጣይነት ያለው ም     ምፅዋት ፣ ሰዎች የሚጠቀሙበት እውቀት እና (ለሞቱት) ዱአ የሚያደርግላቸው ልጅ ናቸው።››

9 ወላጆች ከሞቱ በኋላ ጓደኞቻቸውን እናወዳጆቻቸውን ማክበር ያስፈልጋ። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 2552)

‹‹የመልካምነት ምርጡ ተግባር የአባቱን ወዳጆች (ጓደኞችን) በደግነት መንከባከቡ ነው።››

ከወላጆች ጋር በሚኖራችሁ መስተጋብር ልትከተሏቸው የሚገቡ ስነ-ስርአቶች

  1. በሚያወሩ ጊዜ ልብ ብሎ በጥሞና ማዳመጥ እና ስልክ እየነካኩ ትኩት አለመንፈግ።
  2. ከመጠየቃቸው በፊት የሚወዱትን ነገር ማድረግ ያስፈልጋል። የሚረብሻቸው እና የሚስጨንቃቸው ነገር ወደ እነሱ ከመምጣቱ በፊት ሁሉንም ነገር አድርጎ መመለስ ግድ ነው።
  3. ለጥሪያቸው ምላሽ ለመስጠት ተቻኮል። ወደ እነሱ በመምጣትህ ደስታህን አሳያቸው።
  4. አሏህን ያለመታዘዝ ተግባር ሲፈፅሙ ባየህ ጊዜ የውዴታህን እና የጥበብ የተሞላበት ምክርህን ለግሳቸው።
  5. ወላጆች በደል በሚያደርሱብህ ጊዜ የደግነት ፣ የትዕግስት እና የአክብሮት መልስ ስጥ።
  6. ከእነሱ ተፃራሪ አቋም አትያዝ፤ ፈተናንም አታድርግባቸው።
  7. ፊታቸው ላይ ፈገግታ እንዲኖር አድርጉ።
  8. በግላዊ ጉዳያቸውም ቢሆን አማክራቸው። ሃሳብ አስተያየታቸውን አክብር።
  9. ከእነሱ ጋር አውራ ፣ ተጫወት ፣ የሚያስደስታቸው ከሆነ በእለት ተዕለት የኑሮ ጉዳይ ቢሆንም እንኳ ከእነሱ ጋር ተውያይ።
  10. በጉዞ ምክኒያት ብትለያዩ ዘወትር ደውለህ አግኛቸው። ደህንነታቸውንም ጠይቅ።
0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ የወላጆች መብት

‹‹የወላጆች መብት›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 አብዱሏህ ቢን መስኡድ (ረ.ዐ) ባስረተላለፈው ሐዲስ መሰረት አሏህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆነው ተግባር በቅደም ተከተል የተቀመጠው የትኛው ነው?

2 / 6

Bookmark question icon

2 ትክክለኛ መልሶችን ምረጥ፡ ልጅ በወላጆቹ ላይ ያለበት ግዴታ ምንድን ነው?

3 / 6

Bookmark question icon

3 ትክክለኛ መልሶችን ምረጥ፡ ከወላጆች ጋር በሚኖር መስተጋብር ልትከተሏቸው ከሚገቡ ስነ-ስርአቶች መካከል

4 / 6

Bookmark question icon

4 ወላጆችን ማክበር ያስፈልጋል። ነገርግን የእርጅና እድሜ ላይ በደረሱ ጊዜ ይህን ማድረጉ አያስፈልግም። ምክኒያቱም አስተሳሰባቸው ከወቅቱ ጋር ተራማጅ አይሆንምና።

5 / 6

Bookmark question icon

5 ሃያሉ አሏህ የወላጆችን ሐቅ ያደረገው _____

6 / 6

Bookmark question icon

6 የፈቃደኝነት ጅሃድ ወላጆችን ከማክበር እና ከማገልገል ይቀድማል።

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share