Ahmed Yesuf

This is Ahmed Yesuf, a Sociology graduate who currently works in the culture and tourism office. Writing, reading, and blogging are not just my interests and hobbies, they are my passions. I am proud to have authored 25 Islamic booklets and translated an encyclopedia of Islam specifically for Muslim youth through my educational website. As a dedicated writer and advocate for education, my goal is to continue sharing knowledge, sparking conversations, and making a positive impact in the literary world and beyond.

እውነትም ያልገባው

ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤ የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤ አሏህ አልፈጠረም አንዳች ነገር፤እንዲኖር እንጂ በሱ ትዕዛዝ ስር፤ ከፍጥረታት በሙሉ፤ከአድማስ እስከ አድማስ ያሉ፤እፅዋት አራዊቶች ዛፍና ቅጠሉ፤ አላማ አላቸው የመፈጠራቸው፤የአሏህን አንድነት መስካሪዎች ናቸው፤ የተፈጠረበትን አላማ ዘንግቶ፤የአሏህን ራህመት ቀና መንገድ ትቶ፤ ነፍሱን ተከተለ እሮጠ ነጎደ፤በጥፋት ጎዳና ራሱን አዋረደ፤ እሩጦ […]

እውነትም ያልገባው Read More »

ይቺ አታላይ

ዱንያ ዋጋ ቢሷ ከህልም ያላለፈች፤
በእቅድ በምኞት በባዶ የተሞላች

ለከፊሉ እስር ቤት ለቀሪውም ገነት፤
ከፈጣሪዋ ዘንድ እንስ ያለች መሬት፤

አይይቀሬውን ጉዳይ ሞትን አስረስታ፤
በብልጭልጭ ነገር ዳንኪራ አስመትታ፤

ይቺ አታላይ Read More »

ሂጃብሽን ልበሽ ነቅተሽ በዚህ ሰዓት

ውበትሽ ነው ላንቺ ክብር መጠበቂያ፤ወንድ ላይሳሳት ውበት መደበቂያ፤ ቀልቡ እንዳይሰበር ልቡ እንዳይሸፍት፤እባክሽ ልበሽው ጥቅም አለው እህት፤ አይቀርም ቂያማ አብረሽ መጠየቅሽ፤በሠራሽው ጥፋት አብረሽ መቀጣትሽ፤ ስለሂጃብ ጠንቅቀው የማያውቁ፤አስፈላጊ አይደለም ብለው ሲያስወልቁ፤ ጥፋቱ ባንድነው በነሱ አንለጥፈው፤ትልቅ ጥፋትስ ያለው ወደዚህ ነው፤ በቀለም አሸብርቆ ደምቆ አብረቅርቆ፤ከአካልሽ ጋር እንደሙጫ ተጣብቆ፤ ይሄ ሂጃብ አይደል ድሮም አልተባለ፤ያኔ የተባለው የተስተካከለ፤ በጣም ያልደመቀ ያልተጠባበቀ፤በጌጣጌጥ ብዛት

ሂጃብሽን ልበሽ ነቅተሽ በዚህ ሰዓት Read More »

እማየ ውለታሽ ብዙ ነው

እማየ ውለታሽ ብዙ ነው

እናት አለም ክብሬ እማየ አንደቤቴ፤የመኖሬ ዋስትና የዘጠኝ ወር ቤቴ፤በደምሽ ታንፃ መልካሟ ህይወቴ፤ እኔ ስስቅ ስቀሽ ስከፋ ተከፍተሽ፤ሲርበኝ ተርበሽሲጠማኝ ተጠምተሽ፤ በመልካሙ ምኞት መልካሙን አስበሽ፤የወደፊት ተስፋየን ህይወቴን አብርተሽ፤ ለፍተሽ ጥረሽ ግረሽ ደክመሽ አስተምረሽ፤ስሳሳትም መክረሽ ሃሳቤን ቀይረሽ፤ ትክክለኛውን መንገድ መስመሩን አስይዘሽ፤በርካታ ቢሆንም እማየ ውለታሽ፤ውለታሽን ከፋይ ልሆን ቃል ስገባልሽ፤የህይወቴ ብርሃን እማየ እንዳይከፋሽ፤ የትላንቱ ህፃን ዛሬ ሰው ሁኛለሁ፤ክፉና በጎውን ማስታወስ

እማየ ውለታሽ ብዙ ነው Read More »

መሳቅ ወይስ ማልቀስ

መሳቅ ወይስ ማልቀስ

የሰው ልጅ ስሜቱን ከላዩ ሲያነግስ፤ለአሄራ መስራቱን ትቶ ለጀሃነም ሲደግስ፤ሃራምን በመስራት ምድርን ሲያድበሰብስ፤ ያሻውን ሲጠጣ ያሻውን ሲበላ፤ያማረውን ሲወድ ሲፈልግ ሲጠላ፤ሃራምን በመሥራት መልካምን ሲያጥላላ፤እንዲህ ከሆነ ኑሮው ማነለ ከሱ በላይ ተላላ፤ እሱ ዘመናዊ ሆኖ የሸይጧን ተከታይ፤ሰዎችን ለማጥመድ ይላል ከላይ ከታይ፤ ማየቱን ሳይገድብ እስኪበቃው አይቶ፤የስሜት መረቡን እስከ ጫፍ ዘርግቶ፤ ሰው ላየው ለሰማው ሁሉ ከማለለ፤እራሱን የአሏህ ባሪያ ማድረግ ካልቻለ፤በቃ ስሜት

መሳቅ ወይስ ማልቀስ Read More »

ታናሹ ወንድሜ

በጣም የምወደው ታናሹ ወንድሜ፤ይፈካከረኛል ሳይቀር በህመሜ፤ ስበላ ከበላ ሳቆምም ከበቃው፤ሀሙስ ሰኞን ፁሜ ፆምን ላስለምደው፤ረመዷን ሲመጣ ምንም እንዳይከብደው፤ አርሰናል ስለው ማንቼ ካለኝማ፤ለአምስት ወቅት ሰላት ምንም ሳላቅማማ፤ልቁም ይየኝ እስኪ እሱም ይቁማ፤እንዳይጨነቅብኝ በየውመል ቂያማ፤ ፀጉሬን ሳሳድግ ፀጉሩን ካሳደገ፤ሱሪየን ሳስረዝም እሱም ካስረዘመ እኔን በመከተል ሁሉን ካደረገ፤ እስኪ ቁርአን ልቅራ፤እሱም እንዲቀራ፤እንዲሰለፍልኝ ከአዋቂዎች ጎራ፤ሐዲሶችን ላንብብ ሁኜ ከሱጋራ፤አንድ ላይ አንድንሆን በጀነቱ ስፍራ፤

ታናሹ ወንድሜ Read More »

ከሙዕሚን ባህሪ

ከክፉ የራቀለኸይር የታጠቀ ለአኺራ የሚተጋለኸቲማው የሚሰጋ በቀደር ያመነበአደጋ የሰከነ የኔ ብቻ የማይልድክመቱን የሚቀበል ታላቁን አክባሪለታናሹ ራሪ ፈርዱን ቸል ያላለከሱናውም ያለ ንግግሩ ተግባርህይወቱ ቁምነገር ለእምነቱ ሰሪለዲኑ ተቆርቋሪ እውቀትን ፈላጊለበጎ ሁሉ ጓጊ በኑሮው የረጋባለው የተብቃቃ ስሜቱን የገታነፍስያውን የረታ ጏደኞቹ ጥሩአሏህን የሚፈሩ መሞቱን ያወቀቀድሞ የሰነቀ ውሎው ያማረለትኸይር የጨመረበት ለጊዜው የሚሳሳስንፍናን የረሳንዴቱን የያዘለኢብሊስ ያልታዘዘ

ከሙዕሚን ባህሪ Read More »

ጆሮ ዳባ

ለምን ይሆን ጥገኝነትየሰው ድጋፍ ፈላፊነት አንድ ስንዝር ኑ ወደኔጥሩኝ እንጂ እቀበላለሁ እኔ እያለ ሲጣራ በግልፅ በይፋእንዳልሰማን ሆንን ብለን ጀሮ ዳባ አረግንለት ጭራሽ ለአሏህ ሸሪካተውሂድን ወደ ጐን ጣልነው ወደ ጫካ መሸሻ ወዴት ነው ብለን ሳንሰጋሀቅ መስሚያ ጆሮ ልባችን ተዘጋ

ጆሮ ዳባ Read More »

ጓደኛ ፍለጋ

ልቡ ጥሩ አሳቢ ምላሱ የገራ፤ብዙ የሚሠማ ትንሽ የሚያወራ፤ ፊቱ በተዋዱዕ በኢማን ያበራ፤ፈገግታው የሚስብ ከሩቅ የሚጣራ፤ በፈርዱ የቆመ ከሱናውም ያለ፤ደበረኝ ሰለቸኝ ደከመኝ ያላለ፤ ለረጅሙ ጉዞ ጥሩን የሰነቀ፤ለማይቀረው ዓለም መሄዱን ያወቀ፤ ፀባዩ የሚጥም ወግ አመሉ ሸጋ፤እኔስ ሰው ጠፍቶኛል እንሂድ ፍለጋ፤ ልቤን ሰው ሰው አለው የኢማን ጋደኛ፤ቀኑን ፁሞ የሚውል ሌሊቱን የማይተኛ፤

ጓደኛ ፍለጋ Read More »

Scroll to Top