ተቅዋ ማለት የአሏህ ፍራቻ ነው። ተቅዋ ያለው ሰው የሚሰራውን ሁሉ አሏህ ያየኛል ፣ ያውቅብኛል ብሎ የሚጠነቀቅ ነው። ሁልጊዜ በንግግሩ እና በስራው ጥንቁቅ መሆን እና በጎ ስራዎችን በመስራት ከቅጣቱ የአሏህን ጥበቃ የሚሽት ነው።
የአሏህን ትዕዛዛት አጥብቆ መያዝ ፣ ወደ ጀሐነም እሳት የሚመሩ ተግባራትን መራቅ እና ወደ ጀነት የሚመሩ ተግባራትን የሚፈፅም ነው። ሙእሚኖች ተቅዋ እንዲኖራቸው አሏህ ያዛል።
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡194)
አሏህን ፍሩ፤ አሏህ ከሙተቆች ጋር መሆኑንም እወቁ።

ወደ መጭው አለም በሚደረገው ጉዞ በላጩ ስንቅ ተቅዋ መሆኑን አሏህ በቅዱስ ቁርአን ውስጥ እንዲህ ሲል ገልፆታል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡197)
ስንቃችሁን ያ ከስንቅም ሁሉ በላጩ አሏህን መፍራት ነው። የአዕምሮ ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ።
በሌላ የቁረአን አንቀፅ ደግሞ ከሰዎች የተከበረው የአሏህ ፍራቻ በውስጡ ያለው ሰው መሆኑን እንዲህ ሲል ገልፃል
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሑጅራት 49፡13)
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ። ትተዋወቁም ዘንድ ነገዶችና ጎሳዎች አደረግናችሁ። በእርግጥ አሏህ ግልፅ አዋቂ ውስጥንም አዋቂ ነው።
ሙተቆች እንደሚወድ ይጠቅሳል
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ተውባ 9፡4)
በእርግጥ አሏህ ሙተቆችን ይወዳል።
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ሑድ 11፡49)
ታገስም፤ በእርግጥ ምስጉን የሆነችው ፍፃሜ ለሚጠነቀቁ ናት።
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ሷድ 38፡49-51)
ሙተቆች መጨረሻቸው ውብ የሆነች ናት። ይህ ማስታወሻ ነው። አሏህን ፈሪዎች በእርግጥ ውብ የሆነ መመለሻ አላቸው። በራቸው ለእነሱ የተከፈቱ የአድን ጀነት አላቸው። በእርሷ ውስጥ ጋደም ያሉ ሆነው ፍራፍሬዎችን እና መጠጦችን ያዛሉ።


Share