ረሱል መልዕክተኛ ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥር አመልካች ቃሉ ሩሱል የሚለው ነው። ረሱል ማለት አሏህ መልዕክቱን ለማድረስ የመረጠው ፣ ለሰዎች እንዲያስተምር አዲስ ህግ የገለጠለት ሰው ነው።

ረሱል መልዕክተኛ ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥር አመልካች ቃሉ ሩሱል የሚለው ነው። ረሱል ማለት አሏህ መልዕክቱን ለማድረስ የመረጠው ፣ ለሰዎች እንዲያስተምር አዲስ የሸሪአ ህግ የገለጠለት ሰው ነው። አሏህ መልዕክተኞችን የላካቸው ከግልፅ ምልክቶችና ተአምራቶች ጋር ነው።

ከእነዚህ ተአምራቶች መካከል ለነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ወደ እባብነት የምትቀየር በትር እና ለነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) አይነበሲር እና አካል ጉዳተኛ ሆነው የተወለዱትን የማሻል ችሎታ እና በአሏህ ትዕዛዝ ሙታንን ማስነሳት ይገኝበታል።

የተአምራቶች ሁሉ ተአምር አሏህ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለፀላቸው ቅዱስ ቁርአን ነው።

መለኮታዊ

አሏህ መልዕክተኞችን ወደ ህዝቦቻቸው የላከው ከተመሳሳይ መልዕክት ጋር ነው። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ነህል 16፡36)

በእርግጥ በእያንዳንዱ ህዝብ መሃል አሏህን ተገዙ ከጣኦታትም ራቁ በማለት መልዕክተኛን ልከናል።

ጣኦት ማለት ከአሏህ ውጭ የሚመለክ ማንኛውም ነገር ነው። አሏህ በላካቸው መልዕክተኞች ሁሉ ማመን ከስድስቱ የኢማን ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው። አንዳቸውን የካደ ሰው ካፊር (ከሃዲ) ነው።

(ነብይ ፣ ነብዩ ኢሳ ፣ ነብዩ ሙሳ ፣ ሙሐመድ ፣ ኩፍር እና ኢማን ተመልከቱ)

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share