ዊትር የሚለው ቃል በአረብኛ ሙሉ ቁጥር ያልሆነ ማለት ሲሆን በጥቅሉ ሶላተል ዊትርን የሚገልፅ ነው። ዊትር ሶላት ከሌሊቱ ሱና ሶላት በኋላ የሚሰገድ አንድ ረከአ ነው።
በእርግጥ ዊትር ሶላት የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘወትር ተግባር ነበር። ምዕመናን የዘወትር ተግባራቸው እንዲሆንም አጥብቀው አዘዋል። ሆኖም ምዕመናን ችላ ሊሉት አይገባም። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንደህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“የሌሊቱ (ሱና) ሶላት ሊሰገድ የሚገባው በሁለት በሁለት ረከአ ነው። የንጋቱ መቃረብ ከፈራችሁ ዊትር ለማድረግ አንድ ረከአ ስገዱ።”

ሁለት ረከአ ወይም እስከ አስር ረከአ ድረስ መስገድ ሱና ነው። ከዛም አንድ ረከአ ዊትር ሶላት መስገድ። የዊትር ጊዜ የሚጀምረው ከኢሻ ሶላት በኋላ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ ከፈጅር ሶላት በፊት ነው።
በትርሚዚ በተዘገበው ሐዲስ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“አሏህ ዊትር ነው። ዊትርንም ይወዳል።” እንዲህም ብለዋል፡ “ዊትር የስግደታችሁ መጨረሻ (መደምደሚያ) አድርጉ።”
ረከአ እና ተሃጁድ የሌሊት ሶላት ተመልከቱ




Share