የእስልምና ህግ ውስጥ በጥበብ የተሞላ የውርስ ክፍፍል ስርአት አለ፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ኑዛዜ እና ውርስ ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ፡፡

የእስልምና ህግ ሸሪአ አንድ ሙስሊም ሰው ከሞተ በኋላ የሚፈፀም ኑዛዜ እንዲናዘዝ እስልምና ይፈቅድለታል፡፡ በእስልምና ህግ ውስጥ በጥበብ የተሞላ የውርስ ክፍፍል ስርአት አለ፡፡

በዚህ ትምህርት ውስጥ ኑዛዜ እና ውርስ ጋር የተያያዙ አህካሞችን ትማራላችሁ፡፡

የጽሁፉ አላማ

  1. ስለ ኑዛዜ ምንነት ትማራላችሁ፡፡
  2. ስለ ኑዛዜ ክፍሎች እና አህካሞች ትማላችሁ፡፡
  3. ስለ ውርስ ትርጉም ትማራላችሁ፡፡

የኑዛዜ ትርጉም

ኑዛዜ፡ አንድ ሰው ከሞተ ወይም ከሞተች በኋላ የሆነ ነገር እንዲፈፀምለት ሃላፊነት የመስጠትት ጥያቄ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በገንዘቡ መስጅድ እንዲሰሩለት ኑዛዜ መስጠት ነው፡፡

ኑዛዜ

የሆነ ነገር ያገኘ ሙስሊም ሰው ያገኘውን ነገር በተመለከተ ኑዛዜው ሳይፃፍ ሁለት ሌሊቶችን ማሳለፍ ተገቢ አይደለም፡፡ አብዱሏህ ቢን ኡመር (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡

‹‹የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ኑዛዜየ ሳይፃፍ አንዲትን ሌሊት አሳልፌ አላውቅም፡፡›› (ቡኻሪ 2738 ፣ ሙስሊም 1627)

አሏህ በቁርአኑ እንደገለፀው ኑዛዜው የሚፈፈፀመው እና እዳው ሊከፈል የሚገባው ወራሾቹ ድርሻቸውን ከመከፋፈላቸው በፊት ነው፡፡ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 11)

በእሷ ከተናዘዘባት ኑዛዜ ወይም ከዕዳ በኋላ ነው፡፡

የኑዛዜ ሁኔታዎች

ኑዛዜ የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉት፡፡ እነሱም

አስገዳጅ ኑዛዜ

አንድ ሙስሊም ሰው እገዳ ካለበት ወይም የገንዘብ መብት ካለው እና ይህን የሚያሳይ ማስረጃም ሆነ መረጃ ዶክመንት ከሌለው እነዚህን መብቶችን  ለማስጠበቅ ኑዛዜ የግድ መፈፀም አለበት፡፡

ይህ ምክኒያቱም አዳን መመለስ ግዴታ ነውና፡፡ ግዴታው ያለዚህ የሚፈፀም ከሆነም ይህ በራሱ ግዴታ ይሆናል፡፡

የተወደደ ኑዛዜ

ይህ የኑዛዜ አይነት አንድ ሙስሊም ሰው ከሞተ በኋላ ከገንዘቡ ከፊሉን ለበጎ አድራጎት ስራ እንዲውል የሚያደርግበት ነው፡፡ ለምሳሌ ለድሃ ዘመዶች ምፅዋት መስጠትን የመሰለ ነው፡፡ ይህም የተወሰኑ ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡

ሀ) ኑዛዜው ከወራሾቹ መካከል ለአንዱ መሆን የለበትም፡፡ አሏህ ቀድሞ የየድርሻቸውን አከፋፍሏቸዋልና፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 3565 ፣ ትርሚዚ 2120፣ ኢብን ማጃ 2713)

‹‹ለአንድ ወራሽ ኑዛዜ የለውም፡፡››

ለ) ኑዛዜው የገንዘቡ አንድ ሶስተኛ መሆን ይገባዋል፡፡ የገንዘቡ አንድ ሶስተኛ መሆኑ የተፈቀደ ሲሆን ከዛ በላይ ከሆነ ግን የተከለከለ ነው፡፡

ከሶሃቦች መካከል አንዱ አንድ ሶስተኛውን ለመናዘዝ በፈሎገ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከለከሉና እንዲህ አሉ፡

‹‹አንድ ሶስተኛ፤ አንድ ሶስተኛ በጣም ብዙ ነው፡፡›› (ቡኻሪ 2744 ፣ ሙስሊም 1628)

ሐ) ኑዛዜ የሚያደርገው ባለጠጋ እና ለወራሾቹ የሚተወው ገንዘብ በቂ መሆን አለበት፡፡ ሰኢድ ቢን አቢወቃስ (ረ.ዐ) ኑዛዜ ማድረግ በፈለገ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉት፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 1295 ፣ ሙስሊም 1628)

‹‹ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋቸው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው፡፡››

3 የተጠላ ኑዛዜ

ኑዛዜ የሚያደርገው ሰው ትንሽየ ገንዘብ ኖሮት ወራሾቹ በጣም የሚያስፈልጋቸው ከሆነ ነው፡፡ ምክኒያቱም ወራሾቹን ገድቧቸዋልና ነው፡፡

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰአድ ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ ‹‹ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው፡፡›› (ቡኻሪ 1295 ፣ ሙስሊም 1628)

የተከለከለ ኑዛዜ

በእስልና ህግ የተከለከለን ነገር ኑዛዜ እንዲሆን መጠየቅ ነው፡፡ ለምሳሌ ከወራሾቹ ለአንዱ በእድሜ ከፍ ላለው ልጁ እና ለሚስቱ እንዲወርሱት  ፣ መቃብሩ ላይ ጉልላት እንዲሰራለት መጠየቅ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡

የኑዛዜ የህግ ማዕቀፍ

ከኑዛዜው አንድ ሶስተኛውን ለበጎ አድራጎት ስራ መስጠት የተፈቀደ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ መስጠት ግን የተከለከለ ነው፡፡ እንዲያውም መቀነሱ በላጭ ነው፡፡

ሰአድ ቢን አቢወቃስ (ረ.ዐ) እንዲህ ባለ ጊዜ፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! ሁሉንም ገንዘቤን ለበጎ አድራጎት ስራ እንዲውል ትቻለሁ አላቸው፡፡፡ እሳቸውም፡ ‹‹አይሆንም›› እኔም አልኳቸው፡ ግማሽስ፡፡ እሳቸውም፡ አይሆንም አሉ፡፡ እኔም አንድ ሶስተኛስ አልኳቸው፡፡ እሳቸውም፡ አንድ ሶስተኛ፤ አንድ ሶስተኛ ብዙ ነው፡፡ ወራሾችህ ሰዎችን የሚለምኑ ድሃ ከምታደርጋቸው ይልቅ ባለጠጋ ብታደርጋቸው በላጭ ነው አሉ፡፡›› (ቡኻሪ 2742)

ወራሽ ለሌለው ሰው ከአንድ ሶስተኛው ይልቅ ሁሉንም ገንዘቡን ለማውረስ መናዝ የተፈቀደ ነው፡፡

ኑዛዜው ሚፈፀምበት አግባብ

የሟቹን ሰው ኑዛዜ መፈፀም ግዴታ ነው፡፡ ይህ ሃላፊነት የተሰጠው ሰው ቅድመ ሁኔታዎች እስከተሟሉ ድረስ ኑዛዜውን የማይፈፅም ከሆነ ሃጢያት እየሰራ ነው፡፡ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 181)

ኑዛዜውን ከሰማ በኋላ የለወጠ ሰው፤ ሃጢያቱ በነዚያ በለወጡት ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርግጥ አሏህ ሰሚ እና አዋቂ ነውና፡፡

ውርስ

አንድ ሰው በህይወት እያለ የሰበሰበው ገንዘብ በሞተ ጊዜ የዛ ገንዘብ ባለቤት አይሆንም፡፡ ሆኖም የሟቹን ሰው እዳ ከከፈልን እና ኑዛዜውን ከፈፀምን በኋላ ውርሱ ለሚገባቸው ሰዎች ድርሻቸውን ምናከፋፍልበትን ህግ እስልምና ደንግጓል፡፡

ቅዱስ ቁርአን እና የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ውርሱን በወራሾች መካከል አለመግባባት እና ቅራኔ በማይኖርበት አኳኋን የምናከፋፍልበትን ዘዴ ያብራራልናል፡፡ የእስልምና የውርስ ስርአት ከሁሉም የህግ ስርአቶች ሁሉ በላጭ እና በጥበብ የተሞላ ነው፡፡

ሆኖም አንድ ሰው የአንድን ሐገር የህግ ስርአት እና የህዝቡን የአኗኗር ዘይቤ ሰበብ አድርጎ ይህን የሸሪአ የህግ ስርአት መቀየር አይፈቀድለትም፡፡ ለዚህም ነው ሃያሉ አሏህ ከውርስ አያ በኋላ እንዲህ ያለው፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 13)

እነዚህ የአሏህ ውሳኔዎች ናቸው፡፡ አሏህን እና መልዕክተኛውንም የሚታዘዙ ሰዎች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ያስገባቸዋል፡፡ ይህም ትልቅ ዕድል ነው፡፡

በሟቹ ሰው ልጆች እና ዘመዶች በመካከላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክን እንዳይፈጠር ስለ ሸሪአ የውርስ ክፍፍል  ስርአት ኡለማኦችን እና ፍቅሃዎችን መጠየቅ አለባቸው፡፡

0%
1
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሞት እና ስርአተ ቀብር

ጥያቄና መልስ፡ ኑዛዜ እና ውርስ

‹‹ኑዛዜ እና ውርስ›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ብዙ ሃብት እና ወራሾች ያሉት ሰው ለእነሱ _____ መተው የተፈቀደ ነው፡፡

2 / 6

Bookmark question icon

2 የውርስ ክፍፍል የሚደረገው ሰዎች እንደሚኖሩበት ቦታ ባህል እና ልማድ ነው፡፡

3 / 6

Bookmark question icon

3 አንድ ሃብታም ሙስሊም ከሞተ በኋላ አንድ ሶስተኛውን ገንዘቡ ለድሆች እንዲሰጥ ቢናዘዝ _____

4 / 6

Bookmark question icon

4 የሸሪአ የውርስ ህግ ወራሾች ከውርሱ የየድርሻቸውን እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

5 / 6

Bookmark question icon

5 ሟቹ ትንሽየ ገንዘብ ትቶ ቢሞት እና ወራሾች ደግሞ የግድ የሚያስፈልጋቸው ቢሆን እና አንድ ሶስተኛውን ለእነሱ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁ ሁክሙ ምንድን ነው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 ውርስን ማከፋፈል የሟቹን ሰው ኑዛዜ እና እዳ ከመክፈል ይቀድማል፡፡

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 83%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share