አሹራ በጨረቃ የቀን አቆጣጠር መሰረት የሙሐረም ወር አስረኛ ቀን ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ቀን ይፆሙ ነበር። ሙስሊሞችም በዚህ ቀን እንዲፆሙ ያበረታቱ ነበር።
አሹራ

አሹራ በጨረቃ የቀን አቆጣጠር መሰረት የሙሐረም ወር አስረኛ ቀን ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በዚህ ቀን ይፆሙ ነበር። ሙስሊሞችም በዚህ ቀን እንዲፆሙ ያበረታቱ ነበር።

ኢብን አባስ እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መዲና በደረሱ ጊዜ ይሁዳዎች የአሹራን ቀን እየፆሙ አገኟቸውና ጠየቋቸው

“እየፆማችሁ ያላችሁት ይህ ቀን ምንድን ነው?” እነሱም እንዲህ ሲሉ መልሱላቸው “ይህ የተባረከ ቀን ነው። በዚህ ቀን አሏህ የእስራኤልን ልጆች ከጠላታቸው ፊርአውን አድኗቸዋል። ነብዩ ሙሳ (አሏህን በማመስገን) ፆመውታል አሏቸው።” ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “የሙሳማ ከእናንተ ይልቅ እኔን በጣም ይገባኛል።” እናም ያን ቀን ፆሙ። ሌሎች እንዲፆሙም አዘዙ።” (ቡኻሪ)

ሙሐረም

በተከታዩ አመት ሙስሊሞች የረመዷን ወር እንዲፆሙ አሏህ አዘዛቸው። እናም የአሹራ ቀን ፆም ግዴታ ያልሆነ በምርጫ የሚሰራ ሆነ። ቡኻሪ እንደገለፁት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መካ ውስጥ እያሉ እንኳ ይንን ቀን ይፆሙ ነበር።

በህይወታቸው ፍፃሜ ማብቂያ ላይ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሙስሊሞች ከአይሁዳዎች እራሳቸውን እንዲለዩ ለማድረግ ከበፊቱ ወይም ከበስተኋላው ሌላ ቀን ጨምረው ካልሆነ በቀር ይህንን ቀን ብቻውን እንዳይፆሙ ወሰኑ። እንዲህም አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ኢማሙ አህመድ)

“እስከ ቀጣይ አመት ከቆየሁ (የሙሐረምን) ዘጠንኛውን ከእሱ ጋር እፆማለሁ” አሉ። ነገርግን ተከታዩ አመት ከመምጣቱ በፊት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞቱ። ሙስሊም እንዲህም ብለዋል “የአሹራን ቀን ፁሙ፤ ከቀኑ በፊት ወይም በኋላ ጨምራችሁ በመፆም ከአይሁዳዎች ተለዩ”

ይህን ቀን መፆም ትልቅ ጥቅሞች አሉት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“የአሹራን ቀን መፆም ያለፈውን አመት (ትንንሽ ወንጀሎች) ያብሳል።”

ነገርግን እነዚህ ትንንሽ ወንጀሎች የሚታበሱት አንድ ሰው ከትልልቅ ወንጀሎች ከራቀ ወይም ከሸሸ ብቻ ነው። ኢብነል ቀይም እንዲህ አለ፡

“ረመዷን መፆም እና በቀን አምስት ጊዜ መስገድ በአረፋ እና በአሹራ ቀን ከመፆም በላይ የበለጠ ነው። ምክኒያቱም በረመዷን እና በቀጣዩ ወይም በጁምአ እና በሌላኛው መካከል ያሉ ሃጢትን ከትልልቅ ወንጀሎች እስከራቀ ድረስ ያብሳልና። ነገርግን ትንንሽ ወንጀሎችን ማበስ አይችሉም ትልልቅ ወንጀሎችን እስካልተወ ድረስ።”

አሹራ

ኢድ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share