ነብዩ ኢብራሂም

Author picture
ነብዩ ኢብራሂም ከአሏህ ነብያቶችና መልዕክተኞች መካከል አንዱ ነው። የትልቅ ስብዕና ባለቤት ሲሆን በሁሉም አጋጣሚና ሁኔታ አሏህን ፈሪም ነበር።
ነብዩ ኢብራሂም

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከአሏህ ነብያቶችና መልዕክተኞች መካከል አንዱ ነው። የትልቅ ስብዕና ባለቤት ሲሆን በሁሉም አጋጣሚ እና ሁኔታ አሏህን ፈሪም ነበር።

አንዳንድ ሰዎች የድንጋይ እና የእንጨት ጣኦቶችን ፣ ሌሎቹ ፈለኮችን ፣ ከዋክብትመን ፣ ፀሐይ እና ጨረቃን ሌሎች ደግሞ ንጉሳቸውን እና ገዥዎቻቸውን ያመልኩ ነበር።

የኢብራሂም (ዐ.ሰ) መንፈሳዊ ሃሳብ በጊዜው ከነበሩት ሁሉ በላይ ብዙ ደረጃዎችን ከፍ እንዲል አስችሎታል። እናም እውቀትና ጥበብን ተጠቅሞ ከህዝቦቹ መሃል አሃዳዊነትን በመስበክ ትልቅ ክብርን ተጎናፅፏል። ለአሃዳዊነት እራሱን የሰጠ ነበር።

ህዝቦቹ ትኩረታቸው ልማዳቸውና ባህላቸው ላይ ብቻ ነው። የኢብራሂም አባት ተራ ጣኦት አምላኪ ብቻ አልነበረም። ይልቁንም በእራሱ እጅም ጠርቦ ይሰራቸው ነበር።

በዚህ ክፉ ማህበረሰብ ውስጥ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በእራሱ ቤተሰቦች እና በማህበረሰቡ ላይ ተነሳ።

አሏህ    የኢብራሂም ልብና አዕምሮ ከፈተለት። ከልጅነቱ ጀምሮ ጥበብን ሰጠው። እንዴት ሰው ሃውልት ሰርቶ እራሱ የሰራውን እንዴት ያመልካል ሲል ኢብራሂም (ዐ.ሰ) አሰበ።

የውሸት አማልክቶቻቸው እንኳን ሰዎችን ሊረዱ እራሳቸውን ከጥፋት የማይከላከሉ መሆኑን ሊያሰያቸው እና ሊያሳምናቸው ፈለገ።

የማይረባ ነፍስ የሌለው ድንጋይ በማምለካቸው ሊያሳፍራቸውም በመሻት ለታላቁ በአል ሁሉም ከተማዋን ለቀው ሲወጡ ወደ ቤተ-መቅደሱ በማቅናት ትልቁን ጣኦት ሳይነካ ጣኦቶቹ እንደተጣሉና ትልቁ ጣኦት ሌሎቹን እንደሰባበራቸው አድርጎ አደቀቃቸው።

ወደ ተረፈው ጣኦት በመዞር ይህ ሁሉ እንዴት ሊሆን እንደቻለ ይጠይቁት ይሆን?

ሰዎቹ እንደተመለሱ ጣኦቶቻቸው ድቅቅ ማለታቸውን ተመለከቱ። ሆኖም ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እንዲታሰር ፈለጉ። ጣኦቶቹን ለመሰባበራቸው ተጠያቂ እሱ መሆኑን ሲጠይቁት ትልቁን ጣኦት አልተሰበረም እሱን ጠይቁ፤ ወንጀለኛው እሱ መሆን አለበት አለ።

ጣኦቱ የማይንቀሳቀስ እና የማይናገር መሆኑን ታውቃለህ ሲሉ መለሱለት። በዚህ ምላሽ ነብዩ ኢብራሂም የውሸት ጣኦቶችን ማምለክ ቂልነት መሆኑን የሚያጋልጥበት እድል አገኘ።

ምንም እንኳ የውሸት እምነታቸውን ተቃርኖ ቢረዱም ባቀጣጠሉት ትልቅ እሳት ውስጥ በመወርወር ሊቀጡት ወሰኑ።

ለዚህ አላማ ጥልቅ ጉድጓድ ተቆፍሮ በማገዶ እንጨት ተሞላ፤ እናም አነደዱት። ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ውስጥ ተወረወረ። በአሏህም ትዕዛዝ ብቻ ዳነ።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንቢያ 21፡69)

“አንች እሳት ሆይ! በኢብራሂም ላይ ቀዝቃዛና ሰላም ሁኝ አልን።”

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሰዎች በአሏህ እንዲያምኑ መጥራቱን ቀጠለ። ህዝቦቹን ወደ ቀጥተኛው መንገድ ለመምራት ትልቅ ጥረት አደረገ። እነሱን ለማሳመንም የሚችለውን ሁሉ ሞከረ።

በተጓዘበት ቦታ ሁሉ ሰዎች አንድ እና ብቸኛ እውነተኛ አምላክ የሆነውን አሏህ እንዲያመልኩ አስተማራቸው።

የነብዩ ኢብራሂም ሚስት ሳራ ልጅ ልትፀንስ ማትችል በመሆኗ ሳራ እራሷ የፈቀደችለትን አገልጋዩን ሐጀርን አገባ። ከእሷም ነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ተወለደ። በማስከተልም ሳራ ኢስሃቅን ወለደች።

ሐጀር እና የዘምዘም ውሃ

ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከሚስቱ ሐጀር እና ከልጁ ኢስማኤል ጋር የእርሻ ማሳ እና ውሃ ወደለለበት ዛሬ መካ ከተማ ተብሎ ወደ ሚታወቀው ሸለቆ ተሰደዱ። ነገርግን አሏህ ለእሷና ለልጇ የዘምዘምን ምንጭ አፈለቀላቸው።

ኢብራሂም እና ኢስማኤል ቅዱሱን ቤት ካዕባን ገነቡ። ሁለቱም ለረዥም ጊዜ ሰገዱ፤ ይህን አገልግሎታቸውን እንዲቀበላቸው እና ለፈቃዱ ያጎበደዱ ሙስሊሞች እንዲያደርጋቸው ፣ ከዘሮቻቸው ሙስሊም ህዝቦች ለፈቃዱ ያጎበደዱ እንዲሆኑ ለመኑ።

እንዲሁም ኢብራሂም (ዐ.ሰ) መካ ከተማ የሰላም ከተማ እንዲያደርጋት ፣ ዘሮቹ የዘወትር ሶላት የሚሰግዱ እንዲሆኑና አመስጋኞች እንዲሆኑ ፍሬዎችንም እንዲሰጣቸው አሏህን ለመኑ።

አሏህ (ዐ.ሰ) ለዚህ ዱአ ምላሸ ሰጠ፤ ካዕባን እና የመካን ከተማ ባረከ። ምንም እንኳ የመካ ዳርድንበር ጠፍ እና ድንጋያማ ቢሆንም ለሃብት እና ለቁሳዊ ህይወት ጥሩ ነገሮችንም ይዟል።

እንዲሁም እስካሁን ጊዜ ድረስ በአራቱም የአለም ማዕዘናት ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች በካዕባ አቅጣጫ ይሰግዳሉ፤ ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግም ይችን የሰላም ከተማ ይጎበኛሉ።

0%
7
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ስለ ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የሕይወት ታሪክ ምን ያህል ያውቃሉ?

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በኢስላማዊ ታሪክ ውስጥ ካሉ ታላላቅ ስብዕናዎች አንዱ ሲሆኑ ታሪካቸውም በቁርአን እና በሐዲስ ጽሑፎች ውስጥ ተጠቅሷል። ከሕይወታቸው፣ ከቤተሰባቸው እና ከነብይነታቸው እጅግ በጣም ብዙ ኃይለኛ ትምህርቶችን መቅሰም ይቻላል፡፡ ከእነዚህም መካከል ብዙዎቹ በሐጅ ሥርዓቶች ወቅት እንደምናከናውናቸው ያሉትን እስከ ዛሬ ድረስ የምናስታውሳቸው ናቸው።

1 / 22

Bookmark question icon

1 ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የት ተወለዱ?

2 / 22

Bookmark question icon

2 በባቢሎን የነበሩ ሰዎች ነብዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) በጣም ያበሳጫቸው እና ግራ ያጋባቸው ምን ሥራቸው ነበር?

3 / 22

Bookmark question icon

3 የነብዩ ኢብራሂም አባት ስም ማን ነበር?

4 / 22

Bookmark question icon

4 የነብዩ ኢብራሂም አባት ሥራ ምን ነበር?

5 / 22

Bookmark question icon

5 አንድ ቀን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በዋሻ ውስጥ ተገልለው ሰማዩን እየተመለከቱ ስለ አንድ እውነተኛ አምላክ – አላህ – እያሰላሰሉ ነበር። ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሊሆን የሚችል አምላክ ብለው ያላሰቡት ከሚከተሉት ውስጥ የትኛውን ነው?

6 / 22

Bookmark question icon

6 አንድ ቀን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ጣዖታቱን ሰባበሩ። ሕዝቡም “አንተ ነህ ይህን ያደረግከው?” ብለው ሲጠይቋቸው በብልሃት የሰጡት መልስ ምን ነበር?

7 / 22

Bookmark question icon

7 ከሐዲያኑ ነብዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ከሚከተሉት ውስጥ በየትኛው ውስጥ በመክተት ሊቀጧቸው ወሰኑ?

8 / 22

Bookmark question icon

8 ወደ እሳቱ የጣሏቸው እንዴት ነበር?

9 / 22

Bookmark question icon

9 ወደ እሳት በሚወረወሩበት ጊዜ መጥቶ እርዳታ ያቀረበላቸው መልአክ ማን ነበር?

10 / 22

Bookmark question icon

10 የነብዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) እምነት የተገዳደረው እና እራሱ “አምላክ ነኝ” ብሎ ያወጀው ንጉሥ ስም ማን ነበር?

11 / 22

Bookmark question icon

11 በሕዝባቸው ውድቅ ከተደረጉ በኋላ በባቢሎን በነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ያመኑት 2 ሰዎች ብቻ እነማን ነበሩ?

12 / 22

Bookmark question icon

12 ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በመጨረሻ ሃጀርን አገቡ፤ እሷም በግብፅ ለሳራ እንደ ገረድ ተሰጥታ ነበር። ከነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ወንድ ልጅ ወለደች። የልጃቸው ስም ማን ነበር?

13 / 22

Bookmark question icon

13 በእርጅና ዘመናቸው ልጅ እንደሚወልዱ ለኢብራሂም እና ለሳራ መጥቶ ያበሰራቸው ማን ነበር?

14 / 22

Bookmark question icon

14 አላህ ነብዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ከሃጀር እና ከልጃቸው ጋር በአረቢያ ባሕረ ገብ መሬት ወደሚገኝ ሸለቆ እንዲጓዙ አዘዛቸው። በዚያም ምን አደረጋቸው?

15 / 22

Bookmark question icon

15 ሃጀር ለልጇ ምግብ/መጠጥ ለመፈለግ በሁለት ተራሮች መካከል በፍርሃት ትሯሯጥ ነበር። እነዚህ ሁለት ተራሮች ምን ይባሉ ነበር?

16 / 22

Bookmark question icon

16 በእነዚህ ሁለት ተራሮች መካከል ስንት ጊዜ ሮጣለች?

17 / 22

Bookmark question icon

17 አንድ መልአክ መጥቶ መሬቱን ሲመታ የተከሰተው ተአምር ምንድን ነበር?

18 / 22

Bookmark question icon

18 አላህ (ሱ.ወ) ለእሱ ያላቸውን መገዛት ለመፈተን በሕልም ባሳያቸው መሰረት ነብዩ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ምን እንዲያደርጉ አዘዛቸው?

19 / 22

Bookmark question icon

19 ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከዕባን የገነቡት ከማን ጋር ነበር?

20 / 22

Bookmark question icon

20 አንድ ቀን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) አላህ (ሱ.ወ) ሙታንን እንዴት ሕያው እንደሚያደርግ እንዲያሳያቸው ጠየቁ። አላህ (ሱ.ወ) ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) እንዲያርዱ ያዘዛቸውና በመጨረሻም በአላህ (ሱ.ወ) ትእዛዝ ሕያው የሆኑት እንስሳት የትኞቹ ነበሩ?

21 / 22

Bookmark question icon

21 ከነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ጋር የተያያዘ የትኛው ጉልህ ቅርስ ነው እስከ ዛሬ ድረስ በከዕባ አቅራቢያ የሚገኘው እና “መቃመ ኢብራሂም” በመባል የሚታወቀው?

22 / 22

Bookmark question icon

22 አላህ (ሱ.ወ) በቁርአን ውስጥ ከጠቀሳቸው የነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ቅጽል ስሞች አንዱ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 17%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ኢስማኤል ፣ መካ እና ዘምዘምን ተመልከቱ

Related posts

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።

Read More »
ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ) አሏህ የላካቸው በሰሜን ምዕራብ አረቢያ ፣ በመዲና እና በሶሪያ መካከል ይኖሩ ለነበሩ የሰሙድ ህዝቦች ነው። ይህ ቦታ አለታማ እና ትልቅ ለም ሸለቆ

Read More »

Share