ተራዊህ የሚለው ቃል ተራዊሃህ ከሚለው ነጠላ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ‹እረፍት› ማለት ነው። ይህ የተባለበት ምክኒያት ኢማሙ እና ጀመአው ለረዥም ጊዜ ለሶላት ከቆሙና ከተቀመጡ ከአራት ረከአዎች በኋላ የሚያርፉ በመሆኑ ነው።
ተራዊህ በረመዷን ውስጥ ከኢሻ ሶላት በኋላ የሚጀምር የሌሊት ሶላት ነው። ይህን ሶላት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጅድ ውስጥ ለሶሰስት ምሽቶች ያህል ሰግደዋል። ነገርግን እሳቸውን ተከትለው የሚሰግዱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ሲመጣ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ እንዳይሆንባቸው በመፍራት ከቤታቸው ሰግደዋል።
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ከሞቱ ቡኋላ ሰዎች የተራዊህ ሶላት መስገድ ቀጠሉ። አንዳንዶቹ በግላቸው ሲሰግዱ አንዳንዶቹ ደግሞ በጀመአ ይሰግዱ ነበር። ምዕመናን ከኢማሙ ጀርባ ሆነው ይህን ሶላት እንዲሰግዱ የተደረገው በኸሊፋው ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ጊዜ ነው። ኢማሙም ኡበይ ኢብኑ ካአብ (ሰ.ዐ.ወ) ነበር።
በሶላተ ተራዊህ ውስጥ ያለው የረከአ መጠን አስራ አንድ ነው። አቡ ሰላማ ኢብን አብዱ ረህማን ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሌሊት ሶላት በረመዷን ውስጥ ምን እንደሚመስል አኢሻ (ሰ.ዐ.ወ) በጠየቃት ጊዜ
(ቡኻሪ)
“የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) (የሌሊት) ሶላት በረመዷንም ሆነ በሌላ ወራት ፈፅሞ ከአስራ አንድ ረከአ አይበልጥም።” ስትል መልሳለች።
በረመዷን ውስጥ የሌሊት ሶላት መስገድ ታላቅ ምንዳ (ሽልማት) ከአሏህ የሚያስገኝ ተግባር ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“በረመዷን ወቅት ከአሏህ ምንዳ (ሽልማት) እንደሚያገኝ አምኖና ተስፋ አድርጎ የሌሊት ሶላት የሰገደ ሰው ያለፉ ወንጀሎቹ ሁሉ ይማሩለታል።”

ረመዷን ፣ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ እና ረከአ ተመልከቱ




Share