ኡዱሂያ ማለት ወደ አሏህ መቃረብን በመፈለግ ከኢዱል አዱሃ ሶላት በኋላ የሚታረድ ለእርድ የሚሆን እንስሳ ነው። ይህ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘወትር ተግባር ነው። አቅሙ ያለው ሙስሊም ሁሉ ይህን ተግባር መፈደፀም አለበት።
ኡዱሂያ

ኡዱሂያ ማለት ወደ አሏህ መቃረብን በመፈለግ ከኢዱል አዱሃ ሶላት በኋላ የሚታረድ ለእርድ የሚሆን እንስሳ ነው።

ይህ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘወትር ተግባር ነው። አቅሙ ያለው ሙስሊም ሁሉ ይህን ተግባር መፈደፀም አለበት። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐጅ 22፡36)

(በሁጃጆች ለእርድ የሚቀርቡ ላም ፣ በሬ ወይም ግመል) ከአሏህ ምልክቶች አድርገናቸዋል። በእርሷም ለእናንተ መልካም ጥቅም አላችሁ።

ኡዱሂያ

ለአሏህ መሱአት ማቅረብ ለእሱ ያለንን ምስጋና የምንገልፅበት ተግባራዊ ማሳያ እንደሆነም ነግሮናል።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐጅ 22፡36)

ታመሰግኑም ዘንድ ለእናንተ ገራናት (መጠቀሚያ አደረግን)።

የእርድ እንስሳ ማረድ ያሰበ ሰው፤ የዙልሂጃ ወር ቀድሞውኑ የጀመረ ከሆነ እንስሳ ከማረዱ በፊት ጥፍሩን አይቆርጥም ወይም እራሱን አይላጭም ወይም ፀጉሩን አያሳጥርም። እርዱ እስከ ዙልሂጃ አስራ ሶስተኛው ቀን አሱር ሶላት ድረስ ይቀጥላል።

በግ ፍየል

ኡዱሂያ ለምግብነት የሚሆኑ እንስሳ መሆን አለባቸው። ለምሳሌ በሬ ፣ ግመል ፣ በግ ፣ ፍየል ናቸው።

በሬ ወይም ግመል ከሆነ ሰባት ሰዎች እያንዳንዳቸው መስዋዕት እንደሚያደርጉ በማሰብ ሰባቱም በጋራ ሊያደርዱ ይችላሉ።

ግመል

በግ ወይም ፍየል ከሆነ በሁጃጆች እና በቤተሰብ አባሎች ስም መስዋዕት ማድረግ ይችላል። የግመሉ ወይም የወይፈኑ እድሜ ቢያንስ ሁለት አመት መሆን አለበት። ለበግ ቢያንስ ስድስት ወር፤ ለፍየል ደግሞ ቢያንስ አንድ አመት መሆን አለበት።

አንድ አይኑ ወይም ሁለት አይኑ የጠፋ ፣ አካሉ የጎደለ ፣ በጣም የታመመ ወይም ደግሞ በጣም የከሳ ኡዱሂያ እንስሳ ማረድ አይበቃም።

የእርድ እንስሳ መስዋዕት ማድረግ ምንዳው ትልቅ ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡ “በኡዱሂያ ቀን አሏህ ዘንድ በጣም የሚወደደው ተግባር የእርድ እንስሳውን ደም ማፍሰስ ነው።” (ትርሚዚ)

ኡዱሂያ ከታረደው ስጋ የተወሰነውን መብላት ፣ የተወሰነውን ሶደቃ መስጠት እና የተወሰነውን ለጓደኞች እና ለጎረቤቶች መስጠት የተወደደ ነው።

ኡዱሂያ እርድ

ኢድ እና አቂቃ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share