ሸፈአ ማለት ምልጃ ማለት ሲሆን የሚያማልደው ሰው ደግሞ ሻፊእ ተብሎ ይጠራል። ማማለድ ማለት የእራስን የማግባባት አቅም ተጠቅሞ የሆነ ሰው ከቅጣት እንዲድን ወይም ምህረቱን እንዲያገኝ በስልጣን ላይ ያለውን በተማፅኖ ማግባባት ማለት ነው።
ሸፈአ ወይም ምልጃ በፍርዱ ቀን የሚፈፀመው እነዚህ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች ሲሟሉ ነው።
- ለአማላጁ አሏህ እንዲያማልድ ፍቃድ ሲሰጠው ነው።
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡255)
“በፈቃዱ ቢሆን አንጅ ከእሱ ዘንድ የሚያማልድ ማነው”
- አማላጁ የሚያማልድለትን ሰው አሏህ የተደሰተበት፤ የወደደው ከሆነ
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አንቢያ 21፡28)
“እሱ ለወደደው ካልሆነ በቀር አያማልዱም”

በመጭው አለም ህይወት አምስት አይነት ሸፈአዎች አሉ
- ትልቁ ምልጃ ይህ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ብቻ የተወሰነ ነው። አሏህ ቃል የገባላቸው ከፍተኛው ምስጋናና ክብር ነው።
አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢስራዕ 17፡79)
“ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል”
ይህ የሚሆነው በፍርዱ ቀን ሰዎች በጣም ሲቸገሩና አማላጅ ሲፈልጉ ነው። መጀመሪያ ወደ አደም (ዐ.ሰ) ይሄዳሉ ፣ ከዛ ወደ ነብዩ ኑህ (ዐ.ሰ) ፣ ከዛ ወደ ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ፣ ከዛ ወደ ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ፣ ከዛ ወደ ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) ይሄዳሉ። ሁላቸውም ለዚህ ተገቢ እንዳልሆኑ ይናገራሉ።
ነብዩ ኢሳ (ዐ.ሰ) ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲሄዱ በነመገሯቸው ጊዜ ወደ እሱ ይሄዳሉ። እሱም ከአሏህ ዙፋን ስር ይሰግዳሉ። እናም “ሙሐመድ ሆይ! እራስክን አንሳ፤ አማልድም ፤ ምልጃህ ተቀባይነት አለውና። የፈለከውን ነገር ጠይቅ ይሰጥሃል” ይባላሉ። (ቡኻሪ ቁ. 3340 እና ቀ. 7440)

- ያለ ጥያቄ ወደ ጀነት ለሚገቡ አንዳንድ ሰዎች የተሰጠ ምልጃ፡ ይህ ለነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ብቻ የተሰጠ ነው።
- የጀሐንም እሳት ውስጥ መግባት ለሚገባቸው አንዳንድ ሰዎች የሚሰጥ ምልጃ፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና አሏህ የሻለት ሰው ያማልድላቸዋል።
- ጀነት ለገቡ ሃጢያተኞች የሚሰጥ ምልጃ፤ በነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ፣ በመልአክቶች እና በደጋግ የአሏህ ባሮች ምልጃ ምክኒያት አሏህ ከእሳት እንደሚያወጣቸው የሚናገር ሐዲስ አለ።
- ጀነት ውስት ላሉ ሰዎች ደረጃቸውን ከፍ ያደርግላቸው ዘንድ የሚሰደረግ ምልጃ
አደም ፣ ኢብራሂም ፣ ኢሳ ፣ ሙሳ ፣ ኑህ ፣ ሙሐመድ እና የውመል ቂያማ ተመልከቱ


Share