ጀናዛ እና የጀናዛ ሶላት

Author picture
በሞተው ሰው ላይ መስገድ እና አስክሬኑን መቅበር ሟቹ በሙስሊም በወንድሞቹ ላይ ያለው መብት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ሰው  በእስልምና ውስጥ የመከበሩ መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ሶላቱል ጀናዛ እና ከቀብር ጋር የተያያዙ ሁክሞችን ትማራላችሁ፡፡
ጀናዛ እና የጀናዛ ሶላት

በሞተው ሰው ላይ መስገድ እና አስክሬኑን መቅበር ሟቹ በሙስሊም በወንድሞቹ ላይ ያለው መብት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ሰው  በእስልምና የመከበሩ መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ፅሁፍ ውስጥ ስለ ጀናዛ እና የጀናዛ ሶላት እና ከቀብር ጋር የተያያዙ ሁክሞችን ትማራላችሁ፡፡

በዚህ ፅሁፍ

  1. በሞተ ሰው ላይ የሚሰገድ ሶላት ገለፃን ታወቃላችሁ፡፡
  2. ከቀብር ጋር የተያያዙ አህካሞችን ታወቃላችሁ፡፡

ጀናዛ

ጀናዛ

ጀናዛ ማለት የሞተ ሰው ጀሰድ (አካል) ነው። የሞተን ሰው ለቀብሩ በፍጥነት ማዘጋጀት እና ወደ ሚቀበርበት ቦታ ፈጥኖ ወስዶ መቅበር የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና (ተግባር) ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“ጀናዛን ወደ መቃብሩ ፈጥናችሁ ውሰዱ። የሞተው ሰው መልካም ከነበረ እሱን ወደዛ መውሰዳችሁ መልካም ነው። ከዛ የተለየ ከነበረ ክፋትን ከትከሻችሁ ማላቀቁ ጥሩ ነው።”

የሞተው ሰው መታጠብ ፣ መከፈን/መገነዝ አለበት። እንዲሁም የጀናዛ ሶላት ተብሎ የሚጠራ ልዩ ስግደት ይሰገድለታል። ከዛም ይቀበራል። ጀናዛ ተከትሎ መሄድ ምንዳ የሚያስገኝ ተግባር ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ አመስት መብቶች አሉት ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ስርአተ ቀብሩን (ጀናዛውን) ተከትሎ መሄድ ነው ብለዋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህም ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ እና ሙስሊም)

“የአንድ ሙስሊም ስርአተ ቀብር ላይ ለጀናዛው ሶላት እስኪሰገድለት ድረስ (የቆየ/የተገኘ ሰው) አንድ ቂራት ያገኛል። እስከተቀበረበት ጊዜ ድረስ የተገኘ ሁለት ቂራቶችን ያገኛል። የሆነ ሰው “ቂራት ምንድን ነው? ብሎ ጠየቃቸው። ልክ እንደ ሁለት ትልቅ ተራሮች ነው ሲሉ መለሱ።”

በእስልምና ሃይማኖት ሴቶች ስርአተ ቀብሩን እንዲከተሉ ወይም መካነ መቃብሩን እንዲጎበኙ አይፈቀድም።

የጀናዛ ሶላት

የጀናዛ ሶላት በአካባቢው ባለ ሙስሊም ማህበረሰብ ላይ የጋራ ግዴታ ነው፡፡ የጋራ ግዴታ የሆነበት ምክኒያት የተወሰኑ ሰዎች ከሰገዱበት ከቀሪዎቹ ሰዎች ይቅር የሚባሉ በመሆኑ ነው፡፡

ይህን ሶላት የሰገደ ሰው የአንድ ተራራ ያህል መጠን ያለው ሽልማት እንዲሚያገኝ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የምስራች ሰጥተዋል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 1325 ፣ ሙስሊም 945)

‹‹የቀብር ስነ-ስርአት ላይ ተገኝቶ ከዚያም የጀናዛ ሶላት እስከሚሰገድበት ድረስ የቆየ ሰው ከአንድ ቂራት ጋር እኩል የሆነ ምንዳ (ሽልማት) ያገኛል፡፡ እስኪቀበር ድረስ የቆየ ሰው ደግሞ ከሁለት ቂራት ጋር እኩል  የሆነ ሽልማት ያገኛል፡፡›› ‹‹ሁለት ቂራት ምንድን ናቸው? ተብለው ተጠየቁ፡፡ እሳቸውም፡ ‹‹ልክ እንደ ሁለት ትልልቅ ተራሮች ያሉ ናቸው ሲሉ መለሱ፡፡››

የቀብር ስነስርአት ላይ የመገኘት ጥቅሞች

የቀብር ስነ-ስርአት ላይ መገኘት እና አስክሬኑን መሸኘት ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል የሟቹን ሰው መብት በእሱ ላይ መስገድ ፣ ለእሱ ዱአ ማድረግ ፣ የቤተሰቦቹን መብት መጠበቅ ፣ ሟች ዘመዳቸውን ስላጡ እንዲፅናኑ ማድረግ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡

በቀብር ስነ-ስርአት ላይ የተገኘ ብዙ ሽልማቶችን ያገኛል፡፡ የቀብር ስነ-ስርአት ላይ በመገኘት ፣ ስነ-ስርአቱን በማየት እና ወደ መቃብሩን በመዘየር ግሳፄን እና ትልቅ ሽልማት ያገኛሉ፡፡

የጀናዛ ሶላት አሰጋገድ

የጀናዛ ሶላት አሰጋገድ
  1. የጀናዛ ሶላት በጀመአ (በህብረት) መስገዱ የተወደደ ነው፡፡ ልክ የጀመአ (የህብረት) ሶላት ላይ እንደሚደረገው ኢማሙ ፊት ለፊት ላይ ይቆማል፡፡
  2. የሟቹ ሰው አስክሬን በሚሰገዱት ሰዎች እና በቂብላ መካከል እንዲቀመጥ ይደረጋል፡፡ ኢማሙም በሰውየው ጭንቅላት ትይዩ እና ሴት ከሆነች ደግሞ በወገቧ ትይዩ ይቆማል፡፡ (አቡዳውድ 3194)
  3. የጀናዛ ሶላት አራት ተክቢራዎች አሉት፡፡፡ እነሱም

የመጀመሪያው ተክቢራ

ሰጋጁ እጆቹን እስከ ትከሻው ድረስ ከፍ አድርጎ ያነሳል ወይም እስከታችኛው የጆሮው ክፍል ድረስ ከፍ በማድረግ የመጀመሪያውን ተክቢራ ‹‹አሏሁ አክበር›› ይላል፡፡

ከዚያም የቀኝ እጁን የግራ እጁ ላይ አደራርቦ ደረቱ ላይ ያስቀምጣል፡፡ የሶላት የመክፈቻ ዱአ ሳያነብ የአሏህን ከለላ በመሻት ስሙን ጠቅሶ እና ድምፁን ዝቅ አድርጎ ሱረቱል ፋቲሃን ያነባል፡፡

ሁለተኛው ተክቢራ

ከዚያም ሁለተኛውን ተክቢራው ለሁለተኛ ጊዜ ‹‹አሏሁ አክበር›› ይላል፡፡ ከዚያም በኋላ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ላይ ሰለዋት ያደርጋል፡፡

‹‹አሏህ ሆይ! በነብዩ ሙሐመድ ላይ ሰላም እና በረከትን አድርግ›› በማለት ሰለዋት ያደርጋል፡፡ ሙሉ ቃሉን የሚጠቀም ከሆነ ደግሞ የመጨረሻውን ተሸሁድ ያነባል፡፡

ይህም እንደሚከተለው ነው፡፡ አሏህ ሆይ! በሙሐመድ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ እዝነትህን አድርግ፤ በኢብራሂም እና በቤተሰቦቻቸው ላይ እዝነትህን እንዳሰፈንከው ሁሉ። በእርግጥ! አንተ ምስጉንና ልኡል ነህ። አሏህ ሆይ! በሙሐመድ እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ረድኤትህን አስፍን፤ በኢብራሂም እና በቤተሰቦቻቸው ላይ ረድኤትህን እንዳሰፈንከው ሁሉ። በእርግጥ! አንተ ምስጉን እና ልኡል ነህ።” (ቡኻሪ)

ሶስተኛው ተክቢር

ከዚያም ሶስተኛው ተክቢራ ‹‹አሏሁ አክበር›› ብሎ ለሟቹ ሰው ምህረትን ፣ እዝነትን ፣ ጀነትን እና አሏሀ ጀነት ውስጥ ደረጃውን ከፍ እንዲያደርግለት እንዲሁም ለቀልቡ እና ለምላሱ የገራለትን ዱአ ያደርጋል፡፡

ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተላለፈ ዱአዎችን ከሸመደደ ያን ማድረጉ በላጭ ነው፡፡

ከእነዚህ ዱአዎች መካከል፡ ‹‹አሏህ ሆይ! ምህረትን ለግሰው፡፡ እዘንለት፡፡ ምቾትን ስጠው፡፡ ይቅር በለውም፡፡ መስተንግዶውን መልካም ፣ ቀብሩን ሰፊ አድርግለት፡፡ በውሃ ፣ በውርጭ እና በበረዶ እጠበው፡፡ ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚፀዳው እሱንም ከወንጀል አፅዳው፡፡ ከነበረበት የበለጠ መኖሪያ ለግሰው፡፡ የተሻለ ቤተሰቦችንም አድርግለት፡፡ ጀነት አስገባው፡፡ ከቀብር እና ከእሳት ቅጣት ጠብቀው፡፡›› (ሙስሊም 963)

አራተኛው ተክቢራ

አራተኛው ተክቢራ ይልና ትንሽ ለእስትንፋሱ እርጋታ በመስጠት በቀኝ ጎኑ ብቻ ተስሊም (አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ) ይላል፡፡

የጀናዛ ሶላት የመስገጃ ቦታ

የጀናዛ ሶላት መስጅድ ውስጥ መስገድ ወይም ደግሞ ለዚሁ አላማ ተብሎ የተመደበ ቦታ ላይ ወይም መካነ መቃብር ውስጥ መስገድ የተፈቀደ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተዘግቧል፡፡

የሟቹን ሰው አስክሬን መሸከም እና አስክሬኑን መከተል

ሱናው ለቀብር ስነ-ስርአት ለማዘጋጀት መቻኮል ፣ በሟቹ ሰው ላይ መስገድ ፣ ወደ መቃብር ቦታው መውሰድ እና መቅበር ነው፡፡ አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 1315 ፣ ሙስሊም 944)

‹‹አስክሬኑን (ለመቅበር) አቻኩሉ፡፡ በጎ (መልካም) ከነበረ ደህንነቱ ወደ ተጠበቀበት እያስተላለፋችሁት ነው፡፡ ይህ ካልነበረ ደግሞ ክፉን ነገር ከትከሻችሁ ማውረድ ነውና፡፡››

ጀናዛውን (አስክሬኑን) የሚከተሉ ሰዎች እሱን በመሸከም ቢሳተፉ እና ቢተጋገዙ የተወደደ ነው፡፡ አስክሬኑን የሚሸኙት ሰዎች ከፊት እና ከኋላ  ሁነው መጓዝ ሱና ነው፡፡ መካነ መቃብሩ ሩቅ ከሆነ ወይም አስክሬኑን መሸከም በጣም ከከበደ በመጓጓዧ ጭኖ ይዞ መሄድ ይፈቀዳል፡፡

ሟቹን ሰው ሲቀብሩ ከግምት ውስጥ ማስገባት የሚያስፈልጉ ነገሮች

  1. ሟቹን ሰው ካጠቡ ፣ ከከፈኑ እና ከሰገዱበት በኋላ ለመቅበር ማቻኮል የተወደደ ነው፡፡
  2. መቃብሩ በአውሬ እንዳይቆፈር እና ጎርፍ እንዳይወስደው አርቆ እና አስፍቶ መማስ የተወደደ ነው፡፡
  3. መቃብሩ በኤል ቅርፅ ሊማስ ይችላል፡፡ ወይም ደግሞ እንደየ ሐገሩ የመሬት አቀማመጥ እና የአፈሩ ፀባይ ተስማሚነት መማስ ይቻላል፡፡
  4. የሟቹን ሰው ፊት ወደ ቂብላ አዙሮ በቀኝ ጎኑ ማስተኛት የተወደደ ነው፡፡
  5. የሚቀብረው ሰው አስክሬኑን ሲያስቀምጥ ‹‹በአሏህ ስም ፣ በአሏህ እና በአሏህ መልዕክተኛ መንገድ›› ማለቱ የተወደደ ነው፡፡ (ትርሚዚ 1046 ፣ ኢብን ማጃ 1550)

1 የአስክሬኑ ማረፊያ ኤል ቅርፅ ሆኖ ጥልቅ ጉድጓድ ሲሆን መሸፈን ያለበት በጭቃ እና ከጭድ ጋር በተቦካ የሸህላ ጡብ ፣ ወፋፍራም የግንድ ጉማጅ ፣ ድንጋዮች ወይም ሌላ መሰል ነገሮችን በመጠቀም ነው፡፡

2 እዚያ ያሉ ሰዎች ሟቹን አፈር ማልበሳቸው የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶስት እፍኝ አፈር መቃብሩ ላይ ያፈሱ ነበር፡፡ (አደርቁጡኒ 1565)

3 ሰዎች እንዳይቀመጡበት እና እንዳይረማመዱበት ለማድረግ መቃብሩን ሁለት ሳንቲ ሜትር ከፍ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ በዚህ ላይ ግንባታ ማካሄድ የተከለከለ ነው፡፡

ምክኒያቱም ሟቹን ለማላቅ ፣ ከፍ ከፍ ላማድረግ እና በአሏህ ላይ ለማሻረረክ ሰበብ ነውና፡፡

ከተቀበረ በኋላ

የቀብር ስነ-ስርአት ላይ የተገኙ ሰዎች ለሟቹ የአሏህን እዝነት እና ምህረት መለመንናቸው የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 3221)

‹‹ለወንድማችሁ ምህረትን ለምኑለት፡፡ እንዲረጋገጥለትም ጠይቁለት ፣ አሁን እሱ እየተጠየቀ ነውና አሉ፡፡››

Related posts

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡

Read More »
ሱጁድ

ሱጁድ

ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣

Read More »
ኢቃም

ኢቃም

ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ

Read More »
ረከአ

ረከአ

እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share