የእምነት ምሰሶዎች (አርካኑል ኢማን)

Author picture

መንፈሳዊ የአምልኮ ተግባራት የእምነት ምሰሶዎች ወይም አርካኑል ኢማን ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሆኖም ስድስት የእምነት ምሰሶዎች አሉ፡፡ እነሱም የሚከተሉት ናቸው፡፡

01 በአሏህ ማመን

በአሏህ ማመን ማለት ህልውናውን ማመን ፣ ሊመለክ የሚገባው እሱ ብቻ መሆኑን ፣ በጌታነቱ (ሩቡቢያ) ፣ ባላንጣ የሌለው መሆኑን እና አምልኮ የሚገባው እሱ ብቻ መሆኑነህ (ኡሉሂያ) ፣ ውብ ስምና ባህሪያቶች ያሉት መሆኑን ማመን ነው፡፡

እሱ የዚህ ፍጥረተ አለም ፈጣሪ ነው፡፡ የፍጥረተ አለሙ ሁሉ አስተናባሪ ነው፡፡ የሚሆነው እሱ የሻው ነው፡፡ ሊመለክ የሚገባውም እሱ ብቻ ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢህላስ 112፡1-4)

“በል! እሱ አሏህ አንድ ነው፡፡ አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው፡፡ አልወለደም፤ አልተወለደም፡፡ ለእሱም አንድም ቢጤ (አምሳያ) የለውም፡፡”

02 በአሏህ መልአክቶች ማመን

ይህም መልአክቶች አሉ ብሎ ማመን ነው፡፡ ትክክለኛ ቁጥራቸው ከአሏህ በቀር የሚያውቅ የለም፡፡ የፈጠራቸውም እሱን እንዲገዙ እና እንዲያመልኩ ነው፡፡

አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኒሳዕ 4፡172)

“መሲሁ (እየሱስ) የአሏህ ባሪያ ከመሆን ፈፅሞ አይጠየፍም፡፡ (ለአሏህ) የቀረቡት መልአክትም አይጠየፉም፡፡”

መልአክቶች የአሏህን ልዩ ባህሪያት አይጋሩም፡፡ እንዲሁም ልጆቹ አይደሉም፡፡ ይልቁንም አሏህ የፈጠራቸው የተወሰኑ ተግባራትን እንዲፈፅሙ ነው፡፡

አሏህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንቢያ 21፡26-27)

“አረህማን ልጅ ያዘ (አለው) አሉ፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ አይደሉም መልአክቶች የተከበሩ ባሮቹ ናቸው፡፡ በንግግር አይቀድሙትም፡፡ በትዕዛዙም ይሰራሉ፡፡”

03 በአሏህ መጽሐፍት ማመን

መልዕክተኞች የሰው ልጆችን ሁሉ እንዲያስተምሩ አሏህ የገለፀላቸው መለኮታዊ መጽሐፍት አሉ ብሎ ማመን ነው፡፡

እነዚህ መጽሐፍት በተገለፁ (በወረዱ) ጊዜ ከእውነት በስተቀር ምንም አልያዙም ነበር፡፡

እነዚህ መጽሐፍት ሰዎችን ወደ አሏህ አንድነት ጠርተዋል፡፡ እሱ ፈጣሪ ፣ ሉአላዊ ፣ አምልኮ ለእሱ ብቻ የሚገባ እና እሱም ውብ ስምና ባህሪያት ያሉት መሆኑን አስተምረዋል፡፡

ከእነዚህ መጽሐፍት መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • የአብርሃም መጽሐፍ፡ ሱሁፍ ለነብዩ ኢብራሂም (አብርሃም) የተገለፀው መጽሐፍ ነው፡፡
  • ተውራ፡ ተውራ ለነብዩ ሙሳ (ሙሴ) የተገለፀው መጽሐፍ ነው፡፡
  • ዘቡር፡ ዘቡር ለነብዩ ዳውድ (ዳዊት) መጽሐፍ ነው፡፡
  • ኢንጅል (ወንጌል)፡ ኢንጅል ለነብዩ ኢሳ (እየሱስ) የተገለፀው መጽሐፍ ነው፡፡
  • ቅዱስ ቁርአን፡ ቁርአን አሏህ በመልአኩ ጅብሪል አማካኝነት ለነብዩ ሙሐመድ የገለፀላቸው ፍፁም የአሏህ ቃል ነው፡፡ ከእሱ በፊት የነበሩ መጽሐፍትን የሻረ የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐፍ ነው፡፡

ቁርአን ምንድን ነው?

ቁርአን ሙስሊሞች መንፈሳዊ እና የእለት ተዕለት ህይወታቸውን የሚያስተዳድሩበት ህገ-መንግስት ነው፡፡ ከቀደሙት መለኮታዊ መጽሐፍት በሚከተሉት መንገዶች ይለያል፡፡

  • የመጨረሻው መለኮታዊ መጽሐፍ ነው፡፡ በዚህም ምክኒያት እስከ እለተ ፍፃሜ ድረስ አሏህ ሊጠብቀው ቃል ገብቷል፡፡

አሏህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሒጅር 15፡9)

“አስተዋሹ (ቁርአንን) አወረድነው፡፡ በእርግጥም እኛ እንጠብቀዋለን፡፡”

ቁርአን ምንድን ነው?
  • ቁርአን ማህበረሰቡን የሚያሻሽሉ ሁሉንም ህግጋት አካቶ ይዟል፡፡ ተግባር ላይ ሲውል ደግሞ ለሁሉም ደስታን ያረጋግጣል፡፡
  • ቁርአን ከነብዩ አደም እስከ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ድረስ ያለውን የነብያት እና የመልዕክተኞችን ታሪክ ይዟል፡፡
  • ቁርአን የሰው ልጆች ሁሉ ሰላማዊ ህይወት እንዲኖሩ እና ከጨለማ ወጥተው ወደ ብርሃን እንዲሻገሩ የተገለፀ መጽሐፍ ነው፡፡
  • እሱን ማንበብ ፣ መሸምደድ እና ማስተማር የአምልኮ ተግባር ነው፡፡

ስለ ቁርአን ምን ይላሉ?

04 በአሏህ መልዕክተኞች ማመን

አሏህ ከሰው ልጆች መካከል የተመረጡትን መልዕክተኞች አድርጎ እንደ መረጠ ማመን ሲሆን ፍጡራኖቹ እንዲገዙት ፣ ሃይማኖት እና ተውሂድ (አሃዳዊነትን) እንዲያቋቁሙ ከህግጋት ጋር የላካቸው መሆኑን ማመን ነው፡፡

ሆኖም አሏህ መልዕክተኞቹ መልዕክቱን እንዲያስተምሩ ያዘዘ ሲሆን እነሱን ከላካቸው በኋላ በእሱ ላይ የሚያቀርቡት ማስረጃ እንዳይኖር ያደርጋል፡፡

አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንቢያ 21፡7)

“ከአንተም በፊት ወደ እነሱ የምናወርድላቸው የሆኑን ሰዎችን እንጅ ሌላን አላክንም፡፡ የማታውቁም ብትሆኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡”

የመጀመሪያው መልዕክተኛ ነብዩ ኑህ ሲሆን የመጨረሻው መልዕክተኛ ደግሞ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ናቸው፡፡

05 በፍርዱ ቀን ማመን

ይህም የዚህ አለም ህይወት ያበቃል ፣ የሰው ልጅ ሁሉ ለፍርድ ይቀርባል ብሎ ማመን ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ረህማን 55፡26-27)

“በእሷ (በምድር) ላይ ያለ ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ይቀራል፡፡”

አሏህ ሁሉንም ፍጥረት የሚቀሰቅሳቸው ሲሆን ለፍርድም ያቀርባቸዋል፡፡

መልካም ስራ የሰሩትን ፣ በአሏህ ያመኑትን እና ለነብያቶቻቸው እና ለመልዕክተኞቻቸው የታዘዙትን በጀነት ውስጥ ዘላለማዊ ህይወት ይሰጣቸዋል፡፡

እነዚያ የካዱትን እና ለመልዕክተኞቻቸው ያልታዘዙትን ዘላለማዊ በሆነው የጀሐነም እሳት ይቀጣቸዋል፡፡

06 በቀዷ እና ቀደር ማመን

ሁሉም ነገር ከመፈጠሩ በፊት እና ከተፈጠረም በኋላ የሚሆነውን ነገር ሁሉ አሏህ ያውቀዋል ብሎ ማመን ነው፡፡

ወደ መኖር ያመጣቸው በእውቀቱ እና በልኬቱ ነው፡፡ አሏህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ፉርቃን 25፡2)

“ሁሉንም ነገር ፈጠረ፤ በቁርጥ ውሳኔም ወሰናቸው፡፡”

ይህ እምነት አንድ ሰው ነገሮችን ለማግኘት መጣር አለበት ከሚለው እውነታ ጋር አይጋጭም፡፡

ይልቁንም በመለኮታዊ ውሳኔ (በቀደር) ማመን የሚከተሉትን ያስከትላል

  1. በቀዷ እና በቀደር ማመን ንፁህ ህሊና እና የአዕምሮ ሰላም ያስገኛል፡፡ አንድ ሰው በተፈጠረው ወይም ባልተፈጠረው ነገር ላይ ለማዘን ቦታ አይኖረውም፡፡
  2. በዚህ አጥናፈ አለም ውስጥ አሏህ የፈጠራቸውን የነገሮችን እውቀትና ምርምርን ያበረታል፡፡ እንደ በሽታ ያሉ መከራዎች የሰው ልጆች መፍትሄ እንዲፈልጉ ያነሳሳል፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ በዚህ ፍጥረተ አለም ውስጥ አሏህ የመድሃኒት ምንጭ አድርጎ የፈጠራቸውን ነገሮች በመፈለግ ነው፡፡

በአሏህ ላይ መመካትን ይጨምራል፤ ፍጡራኑን ከመፍራት ያድናል፡፡ ኢብን አባስ እንዲህ አለ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ)

‹‹አንድ ቀን ከአሏህ መልዕክተኛ ጀርባ ሆኘ ሳለ እንዲህ አሉኝ፡ ‹አንተ ወጣት ሆይ!የተወሰኑ ቃላትን አስተምርሃለሁ፡፡ የአሏህን ትዕዛዛት ጠብቅ፤ እሱ ይጠብቅሃል፡፡ የአሏህን ትዕዛዛት ጠብቅ፤ ከፊትህ ታገኘዋለህ፡፡ ከጠየክ አሏህን ለምን፡፡ እርዳታ ከፈለክ እርዳታን ከአሏህ ፈልግ፡፡ እወቅ! አለም በሙሉ ሊረዳህ ቢሰበሰብ እንኳ አሏህ ከወሰነልህ በቀር ሊረዱህ አይችሉም፡፡ እንዲሁም አለም በሙሉ ሊጎዳህ ቢሰበሰብ እንኳ አሏህ ቀድሞ የወሰነልህ ካልሆነ በቀር ሊጎዱህ አይችሉም፡፡ ብዕሮቹ ተነስተዋል፤ ወረቀቶቹም ደርቀዋል፡፡››

“በእሷ (በምድር) ላይ ያለ ሁሉ ጠፊ ነው፡፡ የልቅና እና የልግስና ባለቤት የሆነው የጌታህ ፊት ይቀራል፡፡”

(አል-ቁርአን 55፡26-27)

  1. ዶ/ር ሞሪስ ቡካይ የፈረንሳይ የቀዶ ጥገና ሃኪም ፣ ሳይንቲስት ፣ ሊቃውንት እና ጸሐፊ ↩︎

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share