የኡምራ አፈፃፀም
ኡምራ ኢቲማር ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጉብኝት ማለት ነው። ኡምራ በኢህራም ላይ መሆን ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ፣ በሶፋ እና መርዋ መካከል መጓዝ ፣ ራስን መላጨት ወይም ፀጉርን ማሳጠር አጠቃሎ የያዘ ነው።
ኡምራ ኢቲማር ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጉብኝት ማለት ነው። ኡምራ በኢህራም ላይ መሆን ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ፣ በሶፋ እና መርዋ መካከል መጓዝ ፣ ራስን መላጨት ወይም ፀጉርን ማሳጠር አጠቃሎ የያዘ ነው።
ኢህራም ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ለማድረግ መነየት ነው። ምክኒያቱም ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ “የስራዎች ሁሉ ምንዳ መሰረቱ ኒያ ነው” ብለዋልና።
ሐጅ አምስተኛው የእስልምና ምሰሶ ሲሆን በገንዘቡ እና በአካሉ የአሏህን ቤት መጎብኘት የሚችል ሰው በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ይህን የማድረግ ግዴታ አለበት።
አረፋ አረፋት ተብሎ ይጠራል። አረፋ ከመካ በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝ በጣም ሰፊ አውላላ ሜዳ ነው። በሐጅ ወቅት በዙልሂጃ ወር በአስረኛው ቀን ፀሐይ ከወጣች በኋላ እስክትጠልቅ ድረስ ሁጃጆች በዚህ ለጥ ያለ ሜዳ ለአንድ ቀን ይሰባሰባሉ።