ላ ኢላሀ ኢለሏህ፡ የሕይወት ትርጉም እና የደህንነት ቁልፍ
የፍጥረታት ሁሉ ምስጢር፣ የደስታ ምንጭና የጀነት መክፈቻ የሆነችውን “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” የተሰኘችውን ታላቅ ቃል ትርጉም በጥልቀት ይረዱ።
ላ ኢላሀ ኢለሏህ፡ የሕይወት ትርጉም እና የደህንነት ቁልፍ Read More »
የፍጥረታት ሁሉ ምስጢር፣ የደስታ ምንጭና የጀነት መክፈቻ የሆነችውን “ላ ኢላሀ ኢለሏህ” የተሰኘችውን ታላቅ ቃል ትርጉም በጥልቀት ይረዱ።
ላ ኢላሀ ኢለሏህ፡ የሕይወት ትርጉም እና የደህንነት ቁልፍ Read More »
ፍጥረተ ዓለሙ የተገኘበትን ታላቅ ሚስጥር እና የነብያት ሁሉ የጋራ ጥሪ የሆነውን የአላህ አንድነት ምንነት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያግኙ።
የአላህ አንድነት፡ የመፈጠራችን መሰረታዊ ዓላማ Read More »
ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡
ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣ ጣቶችን ከትከሻ ጋር ትይዩ አድርጎ ወደ ቂብላ በመቀሰር ነው። ክንዶች ከወለሉ ከፍ ፣ ከጎን ራቅ ማለት አለባቸው። የእግር ጣቶችን ወለሉ ላይ በመትከል ወደ ቂብላ አቅጣጫ ማዞር ነው። በሱጁድ ወቅት ክርንን
ኢእቲካፍ ማለት ወደ አሏህ የበለጠ ለመቅረብ በማሰብ የረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናትን መስጅድ ውስጥ ተቀምጦ ማሳለፍ ነው። ለይለቱል ቀድር (የድንጋጌው/የውሳኔው ሌሊት) በዚህ ጊዜ ውስጥ ይገኛል። ቅዱስ ቁርአን ይህን ሲገልፅ ከሽህ ወራቶች በላይ በላጭ ነው ይላል። በዚህ ወቅት ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው ለአጭር ጊዜ እና በጣም አስፈላጊ ለሆነ ነገር ብቻ ካልሆነ በቀር መስጅዱን ለቆ መውጣት አይፈቀድም። ለምሳሌ
ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ እንዲል ቢላል ታዟል” ብሏል። (ቡኻሪ)
ለይለቱል ቀድር (የውሳኔው ምሽት) በመጨረሻው የረመዷን አስር ሌሊቶች ውስጥ በአንዱ ሌሊት ውስጥ የሚገኝ ነው። ይህ ምሽት አሏህ ቁርአን ያወረደበት እና በጎ ስራዎችን ከሽህ ወራቶች ስራ በላይ በላጭ ያደረገበት ሌሊት ነው።
እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ በማድረግ ማጎንበስ (ሩኩዕ)
ሩኩዕ ማለት በሶላት ውስጥ የማጎንበስ ተግባር ነው። ጉልቢን እንደሚይዙ ጣቶችን ዘርዘር አድርጎ መዳፉን ጉልበት ላይ በማስቀመጥ ማጎንበስ ነው። ክርኖች ከፊት እና ከጎን በኩል ራቅ ማለት አለባቸው።
ተየሙም እራስን ለሶላት ለማዘጋጀት በማሰብ በውሃ ፈንታ በንፁህ አሸዋ ወይም አፈር ፊትን እና እጅን በማበስ የሚፈፀም ደረቅ ውዱእ ነው። ውሃ ባታገኙ፤ ንፁህ በሆነ የምድር ገፅ ተየሙም አድርጉ። ፊቶቻችሁን እና እጆቻችሁን አብሱ።
ኡምራ ኢቲማር ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጉብኝት ማለት ነው። ኡምራ በኢህራም ላይ መሆን ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ፣ በሶፋ እና መርዋ መካከል መጓዝ ፣ ራስን መላጨት ወይም ፀጉርን ማሳጠር አጠቃሎ የያዘ ነው።
ዊትር የሚለው ቃል በአረብኛ ሙሉ ቁጥር ያልሆነ ማለት ሲሆን በጥቅሉ ሶላተል ዊትርን የሚገልፅ ነው። ዊትር ሶላት ከሌሊቱ ሱና ሶላት በኋላ የሚሰገድ አንድ ረከአ ነው።
ዘካቱል ፊጥር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ የሆነ ምፅዋት ነው። የሚሰጠውም ሊረዱ ለሚገባቸው ሰዎች ሲሆን ረመዷን ተከትሎ በሚመጣው በሸዋል የመጀመሪያ ቀን ላይ ነው። ዘካቱል ፊጥር የኢድ ሶላት ከመስገድ በፊት መሰጠት ይገባል፡፡
ዘካ የአረብኛ የቃል በቃል ትርጉም ማጥራት የሚለው ነው። ዘካ ሶስተኛው የእስልምና ምሰሶ ነው። የሚያስከፍለውን ትንሿን መጠን (ኒሳብ) ለአንድ አመት ሙሉ በያዘ ሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ ነው።
ንፅህና በእስልምና ሃይማኖት የእምነቱ አንድ አካል ነው። ነብዩ ሙሐመድ ሙስሊሞች የግል ንፅህናቸውን የሚጠብቁባቸውን መንገዶች ሁሉ አሳይተዋል። ንፅህናችነን ከምንጠብቅባቸው መንገዶች አንዱ እስቲንጃ ተብሎ ይጠራል።
ተሐጁድ ትርጉሙም የሌሊት ሶላት ማለት ነው። የነብዩ ሙሐመድ የዘወትር ተግባር ነው። የተረጋገጠ የነብዩ ሱና ነው። በአሏህ መንገድ ነፍሳችንን የምናጠራበት ፣ የአሏህ ፍራቻ እና ፅናት የምናበለፅግበት ጥሩ መንገድ ነው።
ኢህራም ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ለማድረግ መነየት ነው። ምክኒያቱም ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ “የስራዎች ሁሉ ምንዳ መሰረቱ ኒያ ነው” ብለዋልና።