የፍላጎት ፆም
የፍላጎት ፆም በተወሰኑ ወቅቶችና አጋጣሚዎች መፆም የተወደደ ነው። ከነዚህም መካከል፦ የአረፋ ቀን መፆም፡ በ9ኛው ዙልሂጃ የሚውል ሲሆን ሀጅ ላይ ያልሆኑ ሰዎች ቢፆሙት ይወደዳል።
የፍላጎት ፆም በተወሰኑ ወቅቶችና አጋጣሚዎች መፆም የተወደደ ነው። ከነዚህም መካከል፦ የአረፋ ቀን መፆም፡ በ9ኛው ዙልሂጃ የሚውል ሲሆን ሀጅ ላይ ያልሆኑ ሰዎች ቢፆሙት ይወደዳል።
ሲያም (ፆም) ማለት የአሏህን ውዴታ በመሻት ፀሐይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ እስከ ምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ግብረ ስጋ ግኑኝነት ከመፈፀም መታቀብ ነው።
ሶላት (ስግደት) በሁሉም ወንድና ሴት ሙስሊሞች ላይ ግዴታ ነው። ሶላት የሃይማኖቱ መሰረት እንደሆነ እስልምና ያስተምራል። ከሸሃዳ (የእምነት ምስክርነት ቃል) ቀጥሎ ሁለተኛው የእስልምና ምሰሶ ነው።
ረመዷን በእስልምና የቀናት አቆጣጠር መሰረት ዘጠንኛው ወር ነው። በዚህ ወር ከንጋት ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ በጥብቅ ይፆማል። ይህን ወር መፆም ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው።
እየሰሱ እውን ፈጣሪ ነውን? አንድ ፍፁም አምላክ ሲባል ደግሞ በሁለንተናዊ ባህሪው ፍፁም አምሳያና ሸሪክ (ተጋሪ) የሌለው ብቸኛ አንድ አምላክ ማለት ነው።
በሞተው ሰው ላይ መስገድ እና አስክሬኑን መቅበር ሟቹ በሙስሊም በወንድሞቹ ላይ ያለው መብት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ሰው በእስልምና ውስጥ የመከበሩ መገለጫ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ሶላቱል ጀናዛ እና ከቀብር ጋር የተያያዙ ሁክሞችን ትማራላችሁ፡፡
ቂብላ ማለት ሁሉም ሙስሊሞች ሶላታቸውን ሲሰግዱ መካ ውስጥ ወደሚገኝ ካዕባ ፊታቸውን አዙረው የሚሰግዱበት አቅጣጫ ነው። ስግደቶች ሁሉ ተቀባይነት አይኖራቸውም ወደ ቂብላ በመዞር ቢሆን እንጅ።
መስጅድ የእስልምና የአምልኮ ቦታ ሲሆን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሙሉ ህይወት የሚያጠነጥነው በዚሁ ዙሪያ ነው። መስጅድ ካለው ጥቅም አኳያ ነብዩ ሙሐመድ ወደ መዲና ከተማ በተሰደዱ ጊዜ የሰሩት የመጀመሪያው መስጊድ መገንባት ነበር።
ሐጅ አምስተኛው የእስልምና ምሰሶ ሲሆን በገንዘቡ እና በአካሉ የአሏህን ቤት መጎብኘት የሚችል ሰው በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ይህን የማድረግ ግዴታ አለበት።
የገላ ትጥበት በአረብኛ ጉሱል ተብሎ ይጥራል። ጉሱል ሙሉ አካልን መታጠብ ነው። ከሶላት በፊት ንፁህ ለመሆን ሙስሊሞች ከፊል ትጥበት ወይም ውዱእ ያደርጋሉ። ነገርግን በአንዳንድ ጉዳዮች የገላ ትጥበት የግድ መደረግ አለበት።
አረፋ አረፋት ተብሎ ይጠራል። አረፋ ከመካ በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝ በጣም ሰፊ አውላላ ሜዳ ነው። በሐጅ ወቅት በዙልሂጃ ወር በአስረኛው ቀን ፀሐይ ከወጣች በኋላ እስክትጠልቅ ድረስ ሁጃጆች በዚህ ለጥ ያለ ሜዳ ለአንድ ቀን ይሰባሰባሉ።
እስልምና ለንፅህና ትልቅ ቦታ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ምክኒት የኢማን ወይም የእምነት ግማሽ እንደሆነ በሐዲስ ተገልፃለ፡፡ ንፅህና ውስጣዊ (መንፈሳዊ) እና ውጫዊ (አካላዊ) ተብሎ ይከፈላል፡፡
ንፅህና በእስልምና ያለው ቦታ Read More »
የረመዷ ወር በጣም ርህሩህ ቸር የሆነው አምላካችን አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ወደ እሱ እንድንቀርብ ፣ ከርሱ ጋር ያለንን ትስስር እንድናጠብቅ ፣ ምህረትን እንድንጠይቅ ፣ ለመጭው አለም ስንቅ እንድንይዝ ፣ ስብዕናችነን እንድናስተካክል ፣ አላማችነን እንድንቀርፅ የሰጠን እድል ወይም ስጦታ ነው።
የረመዷንን ቀናት እንዴት እናሳልፍ? Read More »
የሰው ልጅ ያለ መመሪያና ደንብ ልጓም እንደሌለው ፈረስ በመሆኑ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ የሰው ልጅ መመሪያ ያስፈልገዋል። ሆኖም ፆመኛ ሙስሊም እንደሌሎቹ የእምነቱ ስርአት ሊከተላቸውና ሊተገብራቸው የሚገቡ መመሪያና ደንቦች እንደሚከተለው ተብራርተዋል።
ሶላትን አደራ! ፍርሃት ሲያካብብህ ሀዘን ሲያንዣብብህ እና ትካዜ ሊያስርህ ሲሻ ወዲያውኑ ወደ ሶላት ተነሳ ነፍስህ ትረጋጋለች ፤ ውስጥህም ሰላም ያገኛል።
ረመዳን ሲመጣ “እንኳን አላህ ለረመዳን አደረስን” በማለት ምስጋና እናቀርባለን፤ ነገር ግን ፀጋን ሳይጠቀሙና ሳይጠብቁት በአፍ ብቻ ማመስገን አጉል የሆነ ጨዋታና ትልቅ ክስረት ነው። ይህን የተከበረ የረመዳን ወር ሳንጠቀምበት እንዳያመልጠንና እንዳንከስር የሚረዱንን 100 ምክሮች ናቸው። ✿ ኢማናዊ ምክሮች ➊. ይህ ወር ራስህን የምትመረምርበት፣ ሥራህን የምትገመግምበትና ሕይዎትህን የምታስተካክልበት ወር እንዲሆን ተግተህ ተንቀሳቀስ፤ ➋. ከሰሐባዎችና ከደጋግ ሰለፎች በዚህ
100 ምክሮች ረመዳንን ለመጠቀም Read More »
ከኢየሱስ በፊት እንደነበሩ ነብያቶች ሁሉ የኢየሱስ ወይም የኢሳ (ዐ.ሰ) ሃማኖት እስልምና ብቻ ነው። ኢየሱስም በአንድ አምላክ ብቻ የሚያምን እና አንድ አምላክ ብቻ የሚገዛ ነበር።
ክርስቶስ በክርስትና ውስጥ የት ነው? Read More »