በረካ ማናት 2

ኸድጇ(ረ.ዐ) በረካን እየተመለከተች በረካ ሆይ! ለሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ) ስትይ ወጣትነትሽን መስዋዕት አደረግሽ አሁን ደግሞ እሱ ሊክስሽ ይወዳል። ለሱም ለኔም ስትይ እርጅና ሳይጫጫንሽ አግቢ ትላታለች። በረካም ማንነው የማገባው እመቤቴ? ስትል ትጠይቃታለች።

በረካ ማናት 2 Read More »

አናጢው

አናጢው

አንድ በኮንትራት ተቀጥሮ የሚሰራ፤ በአካቢው የታወቀ የአናጢ ሙያተኛ ነበር። እድሜው እየገፋ በመምጣቱ ጡረታ መውጣት ይፈልጋል። ሆኖም የቤት ግንባታ ስራውን ከዚህ በኋላ እንደሚተው እና ቀሪ ህይወቱን ከቤተሰቦቹ ጋር ማሳለፍ እንደሚፈልግ ለኮንትራት ቀጣሪው ነገረው። ገቢውን ቢያጣም፤ ጡረታ መውጣቱን ፈለገ። አሰሪውም ታታሪ ሰራተኛው ከስራው መውጣቱ የማይቀር እንደሆነ ሲያውቅ

አናጢው Read More »

የአይን ብርሃናችን : አስበህ አመስግን

የአይን ብርሃናችን : አስበህ አመስግን

አንድ አይነበሲር ልጅ ከአንድ ህንፃ መወራረጃ ላይ ኮፍያ ይዞ ተቀምጧል፤ ልጁም አይነበሲርነኝ እባካችሁ እርዱኝ የሚል መልዕክት የያዘ ሲሆን ከኮፍያው ያሉት ሳንቲሞች ትንሽ ነበሩ። አንድ ሰው በጎኑ እየተጓዘ እያለ ከኪሱ ሳንቲሞችን አውጥቶ ኮፍያው አስቀመጠለትና ልጁ የያዘውን መልዕክት አንስቶ በመገልበጥ

የአይን ብርሃናችን : አስበህ አመስግን Read More »

የኢብን ከሲር የህይወት ታሪክ

ኢማድ አድዲን ኢስማኤል ኢብን ኡመር ኢብን ከሲር አል-በስሪ አዲመሽቂ የተወለዱት በ700 ዐ.ሂ ሲሆን አባታቸው የሞቱት የሰባት አመት ልጅ እያሉ ነው። በታላቅ መንድማቸው በመታጀብ ወደ ደማስቆ አቀኑ፤ ብዙ እውቀት ከኢብን ሻኪር አል-አመዲ እና ከለሌሎችም ሻቱ። ከሚታወቁባቸው ስራዎች መካከል አል-ቢዳያ ወኒሃያ(የመጀመሪያው እና የመጨረሻው) ይገኝበታል። የሰኺህ አል-ቡኻሪ ከፊሉን ተንትነዋል

የኢብን ከሲር የህይወት ታሪክ Read More »

አሏህ በፃፈልህ ተብቃቃ ከሁሉም ሰዎች በፀጋ በላጭ ትሆናለህና

አሏህ በፃፈልህ ተብቃቃ ከሁሉም ሰዎች በፀጋ በላጭ ትሆናለህና፡፡ አሏህ በሰጠህ ተክለሰውነት ፣ አቋም ፣ ገንዘብ ፣ ልጅ ፣ ቤትና ችሎታ መብቃቃት ይኖርብሃል። የቁርአንም መልእክት ከዚህ የተለየ አይደለም።

አሏህ በፃፈልህ ተብቃቃ ከሁሉም ሰዎች በፀጋ በላጭ ትሆናለህና Read More »

ኸድጃ የፍቅር ምሳሌ 2

ህልሟ የደስደስ ያለው ነበርና ህልሟን በሰማ ጊዜ ፈገግ አለና ስጋት አይግባሽ ከሰማይ ወርዳ ወደ አጥር ግቢሽ ስትገባ ያየሻት ፀሀይ በተውራት እና በኢንጅል ወደፊት የመጨረሻ ነብይ ሁነው እንደሚላኩ የተተነበየላቸው ነብይን የሚያመላክት ነውና በህይወት ዘመንሽ ታገኝዋለሽ ቤትሽንም ባለሟል

ኸድጃ የፍቅር ምሳሌ 2 Read More »

ታናሹ ወንድሜ

በጣም የምወደው ታናሹ ወንድሜ፤ይፈካከረኛል ሳይቀር በህመሜ፤ ስበላ ከበላ ሳቆምም ከበቃው፤ሀሙስ ሰኞን ፁሜ ፆምን ላስለምደው፤ረመዷን ሲመጣ ምንም እንዳይከብደው፤ አርሰናል ስለው ማንቼ ካለኝማ፤ለአምስት ወቅት ሰላት ምንም ሳላቅማማ፤ልቁም ይየኝ እስኪ እሱም ይቁማ፤እንዳይጨነቅብኝ በየውመል ቂያማ፤ ፀጉሬን ሳሳድግ ፀጉሩን ካሳደገ፤ሱሪየን ሳስረዝም እሱም ካስረዘመ እኔን በመከተል ሁሉን ካደረገ፤ እስኪ ቁርአን ልቅራ፤እሱም እንዲቀራ፤እንዲሰለፍልኝ ከአዋቂዎች ጎራ፤ሐዲሶችን ላንብብ ሁኜ ከሱጋራ፤አንድ ላይ አንድንሆን በጀነቱ ስፍራ፤

ታናሹ ወንድሜ Read More »

መሳቅ ወይስ ማልቀስ

መሳቅ ወይስ ማልቀስ

የሰው ልጅ ስሜቱን ከላዩ ሲያነግስ፤ለአሄራ መስራቱን ትቶ ለጀሃነም ሲደግስ፤ሃራምን በመስራት ምድርን ሲያድበሰብስ፤ ያሻውን ሲጠጣ ያሻውን ሲበላ፤ያማረውን ሲወድ ሲፈልግ ሲጠላ፤ሃራምን በመሥራት መልካምን ሲያጥላላ፤እንዲህ ከሆነ ኑሮው ማነለ ከሱ በላይ ተላላ፤ እሱ ዘመናዊ ሆኖ የሸይጧን ተከታይ፤ሰዎችን ለማጥመድ ይላል ከላይ ከታይ፤ ማየቱን ሳይገድብ እስኪበቃው አይቶ፤የስሜት መረቡን እስከ ጫፍ ዘርግቶ፤ ሰው ላየው ለሰማው ሁሉ ከማለለ፤እራሱን የአሏህ ባሪያ ማድረግ ካልቻለ፤በቃ ስሜት

መሳቅ ወይስ ማልቀስ Read More »

እውነትም ያልገባው

ፍጥረታት በሙሉ ከጥንት ጀምሮ፤መላዕክቶች ሳይቀሩ ኢብሊስን ጨምሮ፤ የሰው ልጅ ሲፈጠር ከአዳም ጀምሮ፤እንዲኖር ነበር ትዕዛዙን አክብሮ፤የአሏህን ሃያልነት ባንድነት መስክሮ፤ አሏህ አልፈጠረም አንዳች ነገር፤እንዲኖር እንጂ በሱ ትዕዛዝ ስር፤ ከፍጥረታት በሙሉ፤ከአድማስ እስከ አድማስ ያሉ፤እፅዋት አራዊቶች ዛፍና ቅጠሉ፤ አላማ አላቸው የመፈጠራቸው፤የአሏህን አንድነት መስካሪዎች ናቸው፤ የተፈጠረበትን አላማ ዘንግቶ፤የአሏህን ራህመት ቀና መንገድ ትቶ፤ ነፍሱን ተከተለ እሮጠ ነጎደ፤በጥፋት ጎዳና ራሱን አዋረደ፤ እሩጦ

እውነትም ያልገባው Read More »

ይቺ አታላይ

ዱንያ ዋጋ ቢሷ ከህልም ያላለፈች፤
በእቅድ በምኞት በባዶ የተሞላች

ለከፊሉ እስር ቤት ለቀሪውም ገነት፤
ከፈጣሪዋ ዘንድ እንስ ያለች መሬት፤

አይይቀሬውን ጉዳይ ሞትን አስረስታ፤
በብልጭልጭ ነገር ዳንኪራ አስመትታ፤

ይቺ አታላይ Read More »

የቀን እና የሌሊት ጊዜያችነን እንዴት ማሳለፍ አለብን?

የቀን እና የሌሊት ጊዜያችነን እንዴት ማሳለፍ አለብን?

ማንኛውም ሰው ህይወቱን በተለያየ መንገድ ያሳልፋል። ነገር ግን ወሳኙ ጥያቄ የህይወቱን ሃቅ የሞላ ወይም የፈፀመ ማነው? የሚለው ነው። እንስሳቶች የህይወታቸውን እያንዳንዷን ጊዜ እንዲሁ ያሳልፋሉ። ነገርግን ጊዜውን በጥበብ የተሰጠው የሰው ልጅ የተለያዩ ነገሮችን በመፈፀም ያሳልፋል።

የቀን እና የሌሊት ጊዜያችነን እንዴት ማሳለፍ አለብን? Read More »

ወጣትነት እና ፍቅር

አንድ ሰው በፍቅር ሊነደፍባቸው የሚችሉ በርካታ ነገሮች አሉ። ለምሳሌ አሏህ ፣ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ፣ የአሏህ ባሮች ፣ እናት ፣ አባት ፣ እህት ፣ ወንድም ፣ ሚስት ወ.ዘ.ተ ነገር ግን ዛሬ ልዳስስ የምንፈልገው እኛ ወጣቶች ከሌላው በተለየ ስለሚያስደስተንና ስለሚፈትነን የፍቅር አይነት

ወጣትነት እና ፍቅር Read More »

ወጣትነት እና መዝናኛዎቻችን

በመጀመሪያ ከቅጥ ያለፈ መዝናናት የሚያስፈልገው ችግር በመኖሩ ምክኒያት ነው። ማለቴ አንድ ሰው መንፈሳዊ ችግር ወይም አለመረጋጋት ካለበት መዝነናናት እንዳለበት ያስባል። ሆኖም ብዙ ችግሮች ሲገጥሙት በዛውልክ ብዙ መዝናናትን ይመርጣል።

ወጣትነት እና መዝናኛዎቻችን Read More »