ተቅዋ የአሏህ ፍራቻ
ተቅዋ ማለት የአሏህ ፍራቻ ነው። ተቅዋ ያለው ሰው የሚሰራውን ሁሉ አሏህ ያየኛል ፣ ያውቅብኛል ብሎ የሚጠነቀቅ ነው። ሁልጊዜ በንግግሩ እና በስራው ጥንቁቅ መሆን እና በጎ ስራዎችን በመስራት ከቅጣቱ የአሏህን ጥበቃ የሚሽት ነው። የአሏህን ትዕዛዛት አጥብቆ መያዝ ፣ ወደ ጀሐነም እሳት የሚመሩ ተግባራትን መራቅ እና ወደ ጀነት የሚመሩ ተግባራትን የሚፈፅም ነው። ሙእሚኖች ተቅዋ እንዲኖራቸው አሏህ ያዛል።














